Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 12:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እያዩህም ግንቡን ቦርቡረው፥ በእርሱም አውጣው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እነርሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ ጓዝህን በዚያ አሹልክ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በሚመለከቱህም ጊዜ የቤትህን ግድግዳ ሸንቁረህ ቀዳዳ አብጅ፤ ዕቃህንም በዚያ ቀዳዳ አሾልከህ አውጣው፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በፊ​ታ​ቸ​ውም ግን​ቡን ነድ​ለህ በዚያ ውጣ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በፊታቸውም ግንቡን ንደል በእርሱም አውጣ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 12:5
5 Referências Cruzadas  

የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።


ቤቶቹን በጨለማ ይሰረስራሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም።


ጓዝህን እንደ ስደተኛ ጓዝ እያዩህ በቀን አውጣው፥ በማታም እያዩህ ስደተኞች እንደሚወጡ እንዲሁ ውጣ።


ለእስራኤልም ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና እያዩህ በትከሻህ ላይ ተሸከመው፥ በጨለማም ይዘኸው ውጣ፥ ምድሪቱንም እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios