Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፀአት 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከሙላትህና ከጭማቂህ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኩር ትሰጠኛለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አታሰማ፤ ወይም የሕዝብህን መሪ አትርገም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አትናገር፤ የሕዝብህንም መሪ አትስደብ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 “ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብንም አለቃ አትርገመው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፀአት 22:28
28 Referências Cruzadas  

ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፥ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ወጣ፤ ስሙ ሺምዒ ሲሆን የጌራ ልጅ ነው፤ እየተራገመም ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።


ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፤ “ይህ የሞተ ውሻ፥ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ።


እኔ አገልጋይህ ኃጢአት መሥራቴን አውቃለሁና፤ እነሆ፥ ዛሬ ግን ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል ከዮሴፍ ቤት ሁሉ የመጀመሪያ ሆኜ መጥቻለሁ።”


የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።


ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፥ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም።


ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለጌታ ስጥ፥ የአንተ ከሆነ ከከብት ሁሉ ተባት ሆኖ አስቀድሞ የተወለደው ለጌታ ይሆናል።


“ማሕፀንን የሚከፈት በኩርን ሁሉ፤ በእስራኤል ልጆች መካከል፥ ከሰውም፥ ከእንስሳም ለእኔ ቀድስልኝ፥ የእኔ ነው።”


አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።


የመከር በዓል፥ በእርሻህ የዘራኸውን የፍሬህን በኵራት፥ ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ በምትሰበስብበት ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።


የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።


የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።


የእስራኤላዊቱም ልጅ የጌታን ስም ሰደበ፥ አቃለለውም፤ ወደ ሙሴም አመጡት። እናቱም ከዳን ነገድ የደብራይ ልጅ ነበረች፥ ስምዋም ሰሎሚት ነበረ።


ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፦ ማናቸውም ሰው አምላኩን ቢሰድብ ኃጢአቱን ይሸከማል።


የጌታንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የአገሩ ተወላጅ ቢሆን፥ የጌታን ስም በሰደበ ጊዜ ይገደል።


በዚያን ጊዜ ጳውሎስ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ! እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።


ጳውሎስም “ወንድሞች ሆይ! ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር፤’ ተብሎ ተጽፎአልና፤” አላቸው።


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤


አሁንም በተመሳሳይ ሁኔታ እነዚህ ሕልመኞች ሥጋን ያረክሳሉ፥ ጌትነትን ይቃወማሉ፥ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ።


ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ሰዎች፥ ‘እነሆ፤ ዳዊት ክፉ ነገር ሊያደርግብህ ይፈልጋል’ ሲሉ ለምን ትቀበላቸዋለህ?


ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ በኀዘን ተመታ።


ዳዊት ግን አቢሳን እንዲህ አለው፤ “አትግደለው! ጌታ በቀባው ላይ እጁን አንሥቶ ከበደል ነጻ የሚሆን ማን ነው?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios