Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 8:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የወደደውን ሁሉ ያደርጋልና ከፊቱ ለመራቅ አትቸኩል፥ ክፉንም በማድረግ አትጽና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ንጉሥ የፈለገውን ማድረግ ስለሚችል ክፉ ዓላማን በመደገፍ አትጽና፤ ከንጉሡም ፊት ለመራቅ አትቸኲል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ጋ​ልና ከፊቱ ሂድ፥ በክፉ ነገ​ርም አት​ቁም፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የወደደውን ሁሉ ያደርጋልና ከፊቱ ትወገድ ዘንድ አትቸኵል፥ ክፉንም በማድረግ አትጽና።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 8:3
13 Referências Cruzadas  

ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”


ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።


ልጄ ሆይ፥ ጌታንና ንጉሥን ፍራ፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ።


በእንስቶች መካከል በድፍረት የሚራመድ አውራ ዶሮ፥ መንጋን የሚመራ አውራ ፍየል፥ በሕዝብ ፊት በግልጥ የሚናገር ንጉሥ።


ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቁጣ የተነሣብህ እንደሆነ ስፍራህን አትልቀቅ።


አንተ እልከኛ፥ አንገትህን የብረት ጅማት፥ ግንባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios