Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መክብብ 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በክፉዎች ላይ የሚደረገው የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው የሚደርስላቸው ክፉዎችም አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከፀ​ሓይ በታች በም​ድር የሚ​ደ​ረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃ​ጥ​ኣን የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸው ጻድ​ቃን አሉ፥ ለጻ​ድ​ቃ​ንም የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ላ​ቸው ኃጥ​ኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኀጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኀጥኣን አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Cópia de




መክብብ 8:14
16 Referências Cruzadas  

በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ እግዚአብሔርንም አላማረረም።


ስለምን ክፉዎች በሕይወት ይኖራሉ? ስለ ምንስ ያረጃሉ? ኃይላቸውንስ ስለምን ያጠነክራሉ?


እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥ ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?”


የክፉዎችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።


ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው፥


የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ ናቸው፥ አላዋቂ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ሆኖም የሁለቱም መጨረሻቸው አንድ እንደሆነ አስተዋልሁ።


ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።


ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ክፉም በክፋቱ ረጅም ዘመን ሲኖር፥ ይህን ሁሉ ከንቱ በሆነ ዘመኔ አየሁ።


አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


አሁንም ትዕቢተኞችን የተባረኩ ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ታንጸዋል፥ እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios