Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በኮሬብም የጌታን ቁጣ ቀሰቀሳችሁ፥ ጌታም ሊያጠፋችሁ እስኪነሳ አስቆጣችሁት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በኮሬብ እግዚአብሔርን ለቍጣ አነሣሣችሁት፤ እርሱም እናንተን ሊያጠፋችሁ እጅግ ተቈጣ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በሲና በረሓ እንኳ እናንተን ለማጥፋት እስኪነሣሣ ድረስ እግዚአብሔርን በብርቱ አስቈጥታችሁታል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በኮ​ሬብ ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ና​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ በእ​ና​ንተ ላይ ተቈጣ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 9:8
7 Referências Cruzadas  

ትእዛዝህን ለማፍረስ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም ሕዝቦች ጋር ለመጋባት እንመለሳለንን? አንተስ ትሩፋን የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቆጣምን?


ጽላቶቹ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፥ በጽላቶቹ ላይ የተቀረው ጽሑፍም የእግዚአብሔር ጽሑፍ ነበረ።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


“ጌታ አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ ‘በዚህ ተራራ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል፤


እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios