Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያስገባሃል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ምንም ነገር የማይታጣባት፣ የዳቦም ዕጦት የሌለባት፣ ዐለቶች ብረት የሆኑባት፣ ከኰረብቶቿም መዳብ ቈፍረህ ልታወጣ የምትችልባት ምድር ናት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ምድሪቱ ሳይጓደልብህ እንጀራ የምትበላባትና ምንም ነገር የማታጣባት ናት፤ ከድንጋዮችዋ ብረት፥ ከኮረብቶችዋም መዳብ ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሳይ​ጐ​ድ​ልህ እን​ጀ​ራን ወደ​ም​ት​በ​ላ​ባት፥ አን​ዳ​ችም ወደ​ማ​ታ​ጣ​ባት ምድር፥ ድን​ጋ​ይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተ​ራ​ራ​ዋም መዳብ ወደ​ሚ​ማ​ስ​ባት ምድር ያገ​ባ​ሃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያገባሃል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 8:9
8 Referências Cruzadas  

አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት።


ዳዊትም ለበሮቹ ሳንቃ ለሚሆኑ ለምስማርና ለመጠረቂያ ብዙ ብረት፥ ከብዛቱም የተነሣ የማይመዘን ናስ አዘጋጀ።


ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ ከቀለጠ ድንጋይም መዳብ ይወጣል።


ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፥ እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል።


ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር ጌታን አምላክህን ትባርካለህ።


የስንዴና ገብስ፥ የወይንና በለስ ዛፍ እንዲሁም ሮማን፥ የወይራ ዛፍና ማር ወደ ሞሉባት ምድር፥


እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”


እዚያ ስትደርሱም ያለ ሥጋት የሚኖር ሕዝብ፥ እግዚአብሔር በእጃችሁ የሚሰጣችሁን አንዳች ነገር ያልጐደላትን ሰፊ ምድር ታገኛላችሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios