Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሥጋውን ቀቅለህ አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሥጋውንም ጠብሰህ አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብላ፤ ሲነጋም ወደ ድንኳንህ ተመልሰህ ሂድ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሥጋውን ቀቅለህ እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ብላው፤ በማግስቱ ወደ ድንኳኖችህ ተመለስ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ትጠ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ታበ​ስ​ለ​ዋ​ለ​ህም፤ ትበ​ላ​ው​ማ​ለህ፤ በነ​ጋ​ውም ተመ​ል​ሰህ ወደ ቤትህ ትሄ​ዳ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ታበስለዋለህ፥ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተነሥተህ ወደ ድንኳንህ ትሄዳለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 16:7
10 Referências Cruzadas  

ይሁን እንጂ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ተከበረ።


የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።


የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።


የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳሉ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤


ነገር ግን ጌታ አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆነው፥ በነገዶቻችሁ መካከል የሚመርጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደ እዚያም ስፍራ ትሄዳላችሁ።


ጌታ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋህ አንዱን እንስሳ ለጌታ ለእግዚአብሔር ፋሲካ አድርገህ ሠዋ።


ነገር ግን አምላክህ ጌታ ለስሙ መጠሪያ በመረጠው ስፍራ ብቻ፥ ፀሐይ ስትጠልቅ ከግብጽ በወጣህበት ቀን የወጣህበትን ሰዓት በመጠበቅ በዚያ ፋሲካን ሠዋ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios