Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 31:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሕዝቅያስም በጌታ ቤት ውስጥ ግምጃ ቤት እንዲያዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ጐተራ እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው፤ እነርሱም አዘጋጁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ንጉሥ ሕዝቅያስም በቤተ መቅደሱ አካባቢ የዕቃ ግምጃ ቤት እንዲዘጋጅ፥ አዞ በተዘጋጀ ጊዜ

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤት ጎተራ ያዘጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጁ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 31:11
6 Referências Cruzadas  

የቤተ መቅደሱን ሕንጻ አስጠግቶ በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ።


ተጨማሪ ሆኖ የተሠራው ሕንጻ የታችኛው ፎቅ መግቢያ በር የሚገኘው ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል ነበር፤ እርሱም ከሁለተኛውና ከሦስተኛው ፎቅ ጋር የሚያገናኙት ደረጃዎች ነበሩት።


ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።


ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios