Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሀያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በመግቢያው በር ያለው በረንዳም ቁመቱ ኀምሳ አራት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ነው፤ ውስጡም በንጹሕ ወርቅ እንዲለበጥ አደረገ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 3:4
6 Referências Cruzadas  

በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።


በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ይቀድሱ ጀመር፥ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ ጌታ ቤት ዋና የመግቢያ ደጅ ደረሱ የጌታንም ቤት በስምንት ቀን ውስጥ ቀደሱት፥ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ።


ወደ ቤቱም መተላለፊያ አገባኝ፥ የመተላለፊያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።


ኢየሱስም በመቅደስ፥ በሰሎሞን ታዛ ይመላለስ ነበር።


እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።


በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios