Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዮዳሄም ሸመገለ፥ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፤ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሣ ዓመት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዮዳሄ ሸምግሎ ዕድሜ ከጠገበ በኋላ፣ በመቶ ሠላሳ ዓመቱ ሞተ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዮዳሄ በዕድሜ እጅግ ከሸመገለ በኋላ በአንድ መቶ ሠላሳ ዓመቱ ሞተ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ኢዮ​አ​ዳም ሸመ​ገለ፤ ዕድ​ሜም ጠግቦ ሞተ፤ በሞ​ተም ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዮዳሄም ሸመገለ፤ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፤ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሣ ዓመት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 24:15
10 Referências Cruzadas  

አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፥ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ።


በመጨረሻዋ እስትንፋሱ አብርሃም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካምም ሽምግልና ሞተ፥ ሸምግሎ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”


ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።


በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ በእርሱም ለጌታ የቤት ዕቃ፥ የአገልግሎትና የቁርባን ዕቃ፥ ሙዳዮቹም፥ የወርቅና የብርም ዕቃ ተሠራበት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር።


በእስራኤልም፥ ለጌታና ለቤቱም ቸርነትን ሠርቶአልና በዳዊት ከተማ ከነገሥታቱ ጋር ቀበሩት።


ዮዳሄም ሁለት ሚስቶች አጋባው፤ ወንዶችና ሴቶችም ልጆች ወለደ።


የእህሉ ነዶ ወራቱ ሲደርስ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥ ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትገባለህ።


የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና።


ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios