Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ ጌታንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮሣፍጥም እጅግ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም ዐወጀ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ፈራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሊፈ​ልግ ፊቱን አቀና፤ በይ​ሁ​ዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 20:3
20 Referências Cruzadas  

ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ነገር ግን የማምለኪያ ዐፀዶቹን ከምድሪቱ አስወግደሃልና፥ ጌታን ለመፈለግ ልብህን አዘጋጅተሃልና መልካም ነገር ተገኝቶብሃል።”


በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።


በዚሁ ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእስራኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብሰውና በላያቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ተሰበሰቡ።


እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር፥ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ሕዝብ ሁሉ በጌታ ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።


ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ቤት ሰብስቡ፥ ወደ ጌታም ጩኹ።


ጌታም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ “እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤


ሰዎቹም ጌታን እጅግ ፈሩ፥ ለጌታም መሥዋዕትን ሠዉ፥ ስእለትንም ተሳሉ።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በጌታ ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።


እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios