Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 30:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋር የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋር አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋራ የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋራ አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ይህንስ ነገር ምን ይሰማችኋል? ነገር ግን የተዋጉትና ዕቃውን የጠበቁት እድል ፈንታ እኩል ይሆናል፥ አንድነት ይካፈላሉ አለ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 30:24
7 Referências Cruzadas  

ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥ የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።


ምርኮውንም ወደ ጦርት ወጥተው በተዋጉትና፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ለሁለት ክፈል።


እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”


የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ እርሱም መሪያቸውም ሆነ። እነርሱም አራት መቶ ያህል ሰዎች ነበሩ።


ዳዊትም ሰዎቹን፥ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።


ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፥ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን ጌታ ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር አስተውሉ፤ ይህን ማድረግ አይገባችሁም።


ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ለእስራኤል እንደ ሕግና ሥርዓት አደረገው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios