Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 14:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በብንያም ግዛት በጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ሠራዊት በየአቅጣጫው መበታተኑን አዩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በብንያም ግዛት በጊብዓ የነበሩ የሳኦል ዘቦች፣ የፍልስጥኤም ሰራዊት በየአቅጣጫው መበታተኑን አዩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሳኦል ወታደሮች የብንያም ግዛት በሆነችው በጊብዓ መሽገው ሁኔታውን ሁሉ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በመታወክ የሚሸሹትን ፍልስጥኤማውያን አዩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ያሉ የሳ​ኦል ዘበ​ኞ​ችም ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ ሠራ​ዊቱ ወዲ​ህና ወዲያ እየ​ተ​ራ​ወጡ ተበ​ታ​ተኑ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በብንያም ጊብዓ ያሉ የሳኦል ዘበኞችም ተመለከቱ፥ እነሆም፥ ሠራዊቱ ወዲህና ወዲያ እየተራወጡ ተበታተኑ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 14:16
8 Referências Cruzadas  

አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥ የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።


እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።


ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም ወንድሙን፥ ባልንጀራም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።


የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።


በሰፈር በእርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።


ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች፥ “ሠራዊቱን ቁጠሩና ማን ከዚህ እንደ ሄደ ለዩ” አላቸው። በቆጠሩም ጊዜ፥ እነሆ፥ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በዚያ አልነበሩም።


ከዚያም ሳኦልና ሰዎቹ ተሰብስበው ወደ ውጊያው ሄዱ። እዚያም ፍልስጥኤማውያን ግራ በመጋባት በታላቅ ትርምስ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ይጋደሉ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios