Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአትን ይሠራል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከዝ​ሙት ራቁ፤ ኀጢ​አት የሚ​ሠራ ሰው ሁሉ ከሥ​ጋው ውጭ ይሠ​ራ​ልና፤ ዝሙ​ትን የሚ​ሠራ ግን ራሱ በሥ​ጋው ላይ ኀጢ​አ​ትን ይሠ​ራል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 6:18
19 Referências Cruzadas  

ወንዱ ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ ዘሩን ቢያፈስስ፥ ሁለቱ በውኃ ይታጠባሉ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩሶች ይሆናሉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እርስ በእርሳቸው ሥጋቸውን እንዲያዋርዱ፥ በልባቸው ፍትወት ለርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው፤


ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።


የሥጋ ሥራም ግልጽ ነው፤ እርሱም ዝሙት፥ ርኩሰት፥ መዳራት፥


ለቅዱሳን የማይገባው፥ ማንኛውም የዝሙትና የርኩሰት፥ ወይም የስስት ነገር ሁሉ በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤


እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤


ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፥ እርሱም መቀደሳችሁ፥ ከዝሙትም መራቃችሁ ነው፤


ይህን ስታደርጉ ግን እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት መሆን የለበትም፤


ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፤ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


ወዳጆች ሆይ! ባዕዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios