Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን ይህን ትእዛዝ ስሰጥ አላመሰግናችሁም፤ ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚሻል ሳይሆን ለሚከፋ በመሆኑ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚጐዳ እንጂ ለሚጠቅም ስላልሆነ፣ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ እያመሰገንኋችሁ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምታደርጉት ክፉ እንጂ መልካም ነገር ስላልሆነ በዚህ አሁን በምሰጣችሁ ትምህርት አላመሰግናችሁም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ይህ​ንም የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ላመ​ሰ​ግ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ ወደ ዝቅ​ተኛ እንጂ ወደ​ሚ​ሻል ግብር አት​ሄ​ዱ​ምና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 11:17
14 Referências Cruzadas  

ግልጽ ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።


ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤


ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።


በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም።


ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።


ማንም የራበው ቢኖር፥ ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ፥ በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር በመጣሁ ጊዜ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።


እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአንድነት በተሰበሰቡበት፥ ሁሉም በልሳን በመናገር ላይ እያሉ፥ እንግዶች ወይም የማያምኑ ሰዎች ወደ ጉባኤው ቢገቡ፥ አብደዋል አይሉምን?


ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።


አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።


ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ለአገረ ገዢዎችም ቢሆን ታዘዙ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios