Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 27:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል የንጉሡን ልጆች ያገለግል ነበረ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 የንጉሥ ዳዊት አጐት የሆነው ዮናታን ብልኅ አማካሪና የታወቀ ምሁር ነበር፤ እርሱና የሐክሞኒ ልጅ ይሒኤል የንጉሡ ልጆች አስተማሪዎች ነበሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 አስ​ተ​ዋ​ይና ጸሓፊ የነ​በ​ረው በአ​ባቱ በኩል የዳ​ዊት አጎት ዮና​ታን አማ​ካሪ ነበረ፤ የአ​ክ​ማ​ኔም ልጅ ኢያ​ሔ​ኤል ከን​ጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 27:32
6 Referências Cruzadas  

ነገር ግን አምኖን በጣም ዘዴኛ የሆነ፥ ዮናዳብ ተብሎ የሚጠራ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ነበር፤


ይህም ሰው እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፥ የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው።


የዳዊትም ኃያላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሦስቱ ኃያላን አለቃ የሐክሞናዊው ልጅ ያሾብዓም ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአንድ ጊዜ ገደለ።


እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።


እነዚህ ሁሉ በንጉሡ በዳዊት ሀብት ላይ ሹሞች ነበሩ።


አኪጦፌልም የንጉሡ አማካሪ ነበረ፤ አርካዊውም ኩሲ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios