Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከእነዚህም ውስጥ የጌታን ቤት ሥራ የሚሠሩት ሀያ አራት ሺህ ነበሩ። ስድስቱ ሺህም አለቆችና ፈራጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺሕ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቈጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺሕ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሡ ከእነርሱ ኻያ አራት ሺህ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን የቤተ መቅደስ ሥራ እንዲያሠሩ መደባቸው፤ ስድስት ሺህ የሚሆኑትን ባለሥልጣኖችና ዳኞች ሆነው እንዲሠሩ መደባቸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ። ስድስቱ ሺህም አለቆችና ፈራጆች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 23:4
16 Referências Cruzadas  

ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።


ኢዮሣፍጥም ከሌዋውያንና ከካህናት ከእስራኤልም የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ በጌታ ስም ፍርድን እንዲፈርዱ በሙግትም ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ በኢየሩሳሌም ሾመ። እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።


ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው፥ እንደ ዳዊትም ትእዛዝ፥ በደስታና በመዝሙር ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በጌታ ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በጌታ ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ።


በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሐፊዎቹና አለቆቹም የደጁም ጠባቂዎች ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።


በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።


አለቃቸውም የዚክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማው ላይ ሁለተኛ የተሾመ ነበረ።


ክርክር በሚነሣበት ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ በፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ፥ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።


የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios