Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 16:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 የኤዶታምም ልጅ ዖቤድ-ኤዶምና ሖሳ የደጁ ጠባቂዎች እንዲሆኑ አድርጎ ከስልሳ ስምንት ወድሞቹ ጋር ዖቤድ-ኤዶምን በዚያ ተወው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 እንዲሁም ዖቤድኤዶምና ስድሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ ዐብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው። የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እነርሱንም እንዲረዱ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ከእርሱ ጐሣ ሌሎች ሥልሳ ስምንት ሰዎች ተመደቡ፤ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ ለቅጽር በሮቹ ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 አብ​ዲ​ዶ​ም​ንም፥ ስድሳ ስም​ን​ቱ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን፤ የኤ​ዶ​ታ​ምም ልጅ አብ​ዲ​ዶ​ምና ሖሳ በረ​ኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋ​ቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 የኤዶታምም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ በረኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋቸው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 16:38
6 Referências Cruzadas  

ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው።


ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢ-ዳራ ቤተሰብ ዘንድ በቤቱ ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም የአቢ-ዳራን ቤትና ያለውን ሁሉ ባረከ።


ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ።


ከሜራሪም ልጆች ለነበረው ለሖሳ ልጆች ነበሩት፤ አለቃውም ሽምሪ ነበረ፤ በኩር አልነበረም፥ አባቱ ግን አለቃ አደረገው፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios