Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ዘካርያስ 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።

2 በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፣ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።

3 ማንም ደግሞ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ አንተ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም ይሉታል፣ ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባቱና እናቱ ይወጉታል።

4 በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል፣ ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።

5 እርሱ ግን፦ ከታናሽነቴ ጀምሮ ባሪያ ሆኜ ነበርሁና ገበሬ ሰው ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም ይላል።

6 ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።

7 ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።

8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

9 ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።

Siga-nos em:



Anúncios