Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ኢዮብ 32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢዮ​ብም በፊ​ታ​ቸው ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና እነ​ዚያ ሦስቱ ወዳ​ጆቹ ለኢ​ዮብ ለመ​መ​ለስ ዝም አሉ።

2 ከአ​ው​ስ​ጢድ ሀገር ከአ​ራም ወገን የሆነ የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤሊ​ዩስ ተቈጣ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና ኢዮ​ብን ተቈ​ጣው።

3 ደግ​ሞም እንደ ኀጢ​አ​ተኛ አደ​ረ​ጉት እንጂ ለኢ​ዮብ የሚ​ገባ መልስ መመ​ለስ ስላ​ል​ቻሉ በሦ​ስቱ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ላይ ተቈጣ።

4 ኤሊ​ዩስ ግን ከእ​ርሱ ይልቅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነበ​ሩና ለኢ​ዮብ መልስ ለመ​ስ​ጠት ጠብቆ ነበር።

5 ኤሊ​ዩ​ስም በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስቱ ሰዎች አፍ መልስ እን​ደ​ሌለ ባየ ጊዜ በቍ​ጣው ተቈ​ጣ​ቸው።

6 የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።

7 እን​ደ​ዚ​ህም አልሁ፥ “የሚ​ና​ገሩ ዓመ​ታት አይ​ደ​ሉም፥ በዓ​መ​ታት ብዛት ሰዎች ጥበ​ብን አያ​ው​ቋ​ትም።

8 ነገር ግን በሟች ሰው ውስጥ መን​ፈስ አለ፥ ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም ያስ​ተ​ም​ራል።

9 በዕ​ድሜ ያረጁ ጠቢ​ባን አይ​ደ​ሉም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ፍር​ድን አያ​ስ​ተ​ው​ሉም።

10 ነገር ግን፦ ስሙኝ፤ እኔ ደግሞ የማ​ው​ቀ​ውን እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ አልሁ።

11 እነሆ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ም​ጡኝ፤ የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር እስ​ክ​ት​መ​ረ​ምሩ ድረስ እየ​ሰ​ማ​ች​ሁት እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።

12 እን​ዲ​ሁም ልብ አደ​ረ​ግሁ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ኢዮ​ብን የገ​ሠጸ፥ ወይም ለተ​ና​ገ​ረው ቃልን የመ​ለሰ የለም።

13 እና​ን​ተም፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ አብ​ዝ​ተ​ና​ልም እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ።

14 እና​ንተ ግን እን​ዲህ ያለ ነገር እን​ዲ​ና​ገር ለሰው መብት ሰጣ​ች​ሁት።

15 “እና​ንተ ፈራ​ችሁ፥ ዳግ​መ​ኛም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም ቁም ነገር ጠፋ።

16 እኔ በት​ዕ​ግ​ሥት ጠበ​ቅሁ እንጂ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም። እና​ንተ ዝም ብላ​ችሁ ቆማ​ችሁ፥ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ምና።”

17 ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ደግሜ እና​ገ​ራ​ለሁ።

18 እኔ ቃል ተሞ​ል​ቻ​ለ​ሁና፥ በው​ስ​ጤም ያለ መን​ፈስ አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛ​ልና።

19 በተሃ ጠጅ እንደ ተሞ​ላና ሊቀ​ደድ እንደ ቀረበ አቁ​ማዳ፥ ወይም እንደ አን​ጥ​ረኛ ወናፍ እነሆ፥ አን​ጀቴ ሆነ።

20 ጥቂት እን​ድ​ተ​ነ​ፍስ እና​ገ​ራ​ለሁ። ከን​ፈ​ሬ​ንም ገልጬ እመ​ል​ሳ​ለሁ።

21 ከሰው የተ​ነሣ አላ​ፍ​ር​ምና፥ ከሟች ሰውም የተ​ነሣ አላ​ፈ​ገ​ፍ​ግ​ምና።

22 ለሰው ፊት ማድ​ላ​ትን አላ​ው​ቅም፤ ከሰ​ውም የተ​ነሣ የማ​ፍ​ረው ካለ ትሎች ይብ​ሉኝ።

Siga-nos em:



Anúncios