Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ኢዮብ 18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የበ​ል​ዳ​ዶስ ንግ​ግር

1 አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦

2 “ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? እኛም እን​ድ​ን​ነ​ግ​ርህ ታገሥ።

3 ስለ ምንስ እንደ እን​ስሳ በፊ​ትህ ዝም አልን?

4 መከ​ራው ይገ​ባ​ሃል፤ አን​ተስ የሞ​ትህ እንደ ሆነ ምን​ድን ነው? ከሰ​ማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችን? ወይስ ተራ​ራ​ዎች ከመ​ሠ​ረ​ታ​ቸው ይና​ወ​ጣ​ሉን?

5 “የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች መብ​ራት ይጠ​ፋል፥ ነበ​ል​ባ​ላ​ቸ​ውም ብልጭ አይ​ልም።

6 ብር​ሃኑ በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ይጨ​ል​ማል፤ መብ​ራ​ቱም በላዩ ይጠ​ፋል።

7 የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ንብ​ረ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ምክ​ሩም ትጥ​ለ​ዋ​ለች።

8 እግሩ በወ​ጥ​መድ ትያ​ዛ​ለች፤ በመ​ረ​ብም ትታ​ሠ​ራ​ለች፤

9 አሽ​ክ​ላ​ዎች በላዩ ይመ​ጣሉ፤ የተ​ጠ​ሙ​ትም በእ​ርሱ ይበ​ረ​ታሉ፤

10 በም​ድር ላይ የሸ​ም​ቀቆ ገመዱ ተሰ​ው​ራ​ለች፤ የሚ​ጐ​ት​ተ​ውም በመ​ን​ገዱ ላይ ነው።

11 መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።

12 ኀይሉ በራብ ትደ​ክ​ማ​ለች። አስ​ጨ​ናቂ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለ​ታል።

13 ጭኖቹ ይበ​ሰ​ብ​ሳሉ። ሞትም መል​ካም ሕዋ​ሶ​ቹን ይበ​ላል።

14 ጤን​ነት ከሥ​ጋው ትር​ቃ​ለች። መከ​ራው ትጸ​ና​ለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ለ​ዋል።

15 በሌ​ሊት በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ለእ​ርሱ የማ​ይ​ሆ​ነው ይኖ​ራል፤ የእ​ር​ሱም መል​ካም ነገር በዲን ይበ​ተ​ናል።

16 ሥሩ ከበ​ታቹ ይደ​ር​ቃል፤ ፍሬ​ውም ከላዩ ይረ​ግ​ፋል።

17 መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጠ​ፋል፤ በም​ድ​ርም ስም አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።

18 ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ አር​ቀው ያፈ​ል​ሱ​ታል።

19 ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሚ​ራ​ራ​ለት የለም፤ ቤቱ ከሰ​ማይ በታች አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።

20 ነገር ግን ባዕድ በን​ብ​ረቱ ላይ ተድላ ያደ​ር​ጋል፤ ድሃው በእ​ርሱ ያጕ​ረ​መ​ር​ማል። ፊተ​ኞ​ቹም ይደ​ነ​ቃሉ።

21 የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ቤት እን​ዲህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የማ​ያ​ውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”

Siga-nos em:



Anúncios