Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ኢዮብ 16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢዮ​ብም መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦

2 “እን​ደ​ዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ የም​ታ​ደ​ክሙ አጽ​ና​ኞች ናችሁ።

3 የመ​ጣ​ላ​ች​ሁን ሁሉ ያለ ልክ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፦ ትከ​ራ​ከ​ሩኝ ዘን​ድስ ምን አስ​ቸ​ገ​ር​ኋ​ችሁ?

4 እኔ ደግሞ እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ና​ገሩ እና​ገር ነበር፤ ነፍ​ሳ​ችሁ በነ​ፍሴ ፋንታ ብት​ሆን ኖሮ፥

5 እኔም ነገ​ርን እነ​ግ​ራ​ችሁ ነበር፤ ራሴ​ንም በእ​ና​ንተ ላይ እነ​ቀ​ንቅ ነበር።

6 ባፌም ኀይል ቢኖ​ረኝ ኖሮ፥ ከን​ፈ​ሬን ባል​ገ​ታ​ሁም ነበር፥ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም ባሻ​ሻ​ልሁ ነበር፤

7 እኔ ብና​ገር ቍስሌ አይ​ድ​ንም፤ ዝም ብልም ሕማሜ ይብ​ስ​ብ​ኛል።

8 አሁን ግን የዕ​ብድ ቍር​ጥ​ራ​ጭና ብጥ​ስ​ጣሽ አደ​ረ​ግ​ኸኝ፤ እኔ​ንም መያ​ዝህ ምስ​ክር ሆነ​ች​ብኝ፤

9 ሐሰ​ቴም በእኔ ላይ ተነ​ሣች፤ በፊ​ቴም ተከ​ራ​ከ​ረ​ች​ብኝ።

10 በቍ​ጣው ጣለኝ፤ ጥር​ሶ​ቹ​ንም አፋ​ጨ​ብኝ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹ​ንም በእኔ ላይ ፈተነ።

11 ዐይ​ኖ​ችን አፍ​ዝዞ ጋረ​ደኝ፤ በተ​ሳለ ጦርም ጕል​በ​ቴን ወግቶ ጣለኝ። በአ​ን​ድ​ነ​ትም ከበ​ቡኝ።

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጠ​ማማ ሰው አሳ​ልፎ ሰጠኝ፤ በክ​ፉ​ዎ​ችም እጅ ጣለኝ።

13 ተዘ​ልዬ ስኖ​ርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕ​ሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላ​ማም አድ​ርጎ አቆ​መኝ፤ እንደ ጉበ​ኛም ተመ​ለ​ከ​ተኝ።

14 በጦር ከበ​ቡኝ፤ ኵላ​ሊ​ቴ​ንም ወጉኝ፤ እነ​ር​ሱም አል​ራ​ሩ​ል​ኝም፤ ሐሞ​ቴ​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ።

15 በው​ድ​ቀት ላይ ውድ​ቀ​ትን አደ​ረ​ሱ​ብኝ፤ ኀያ​ላኑ እየ​ሠ​ገጉ ሮጡ​ብኝ።

16 በቍ​ር​በቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከ​ራዬ በመ​ሬት ላይ በዛች።

17 ሆዴ በል​ቅሶ ተቃ​ጠለ፤ የሞት ጥላን በቅ​ን​ድ​ቦች ላይ አያ​ለሁ፤

18 ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎ​ቴም ንጹሕ ነው።

19 መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?

20 “አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ምስ​ክሬ በሰ​ማይ አለ፤ የሚ​ያ​ው​ቅ​ል​ኝም በአ​ር​ያም ነው።

21 ጸሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትድ​ረስ፥ ዐይ​ኔም በፊቱ እንባ ታፍ​ስስ።

22 የሰው ልጅ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ም​ዋ​ገት፥ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ሟ​ገት ምነው በቻለ!

23 የተ​ቈ​ጠሩ ዘመ​ኖች ደረሱ፤ እኔም ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት መን​ገድ እሄ​ዳ​ለሁ።

Siga-nos em:



Anúncios