Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ኢዮብ 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አየች፤ ጆሮ​የም ሰማች።

2 እና​ንተ የም​ታ​ው​ቁ​ትን እኔ ደግሞ አው​ቃ​ለሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም የም​ሰ​ንፍ አይ​ደ​ለ​ሁም።

3 ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከፈ​ቀ​ደም በፊቱ እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።

4 እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።

5 ላዳ​ም​ጣ​ችሁ አይ​ገ​ባ​ኝም፥ ጥበብ ከእ​ና​ንተ ጠፍ​ታ​ለ​ችና።

6 “አሁን የአ​ፌን ክር​ክር ስሙ፥ የከ​ን​ፈ​ሬ​ንም ፍርድ አድ​ምጡ።

7 በውኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ት​ና​ገሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በፊቱ ሽን​ገ​ላን ታወ​ራ​ላ​ች​ሁን?

8 ከእ​ርሱ ወደ ኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? እስኪ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።

9 እርሱ ቢመ​ረ​ም​ራ​ችሁ መል​ካም ነው፥ ይህን ሁሉ በኀ​ይ​ላ​ችሁ ስታ​ደ​ርጉ ራሳ​ች​ሁን ከእ​ርሱ ጋር አንድ ታደ​ር​ጋ​ላ​ች​ሁና።

10 በስ​ውር ለሰው ፊት ብታ​ደሉ ዘለፋ ይዘ​ል​ፋ​ች​ኋል።

11 ጥን​ቱን ኀይሉ አያ​ስ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ምን? ግር​ማስ ከእ​ርሱ ዘንድ አይ​ወ​ድ​ቅ​ባ​ች​ሁ​ምን?

12 ምሳ​ሌ​ያ​ችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤ ሥጋ​ች​ሁም እንደ ትቢያ ነው።

13 ዝም በሉ፤ እና​ገ​ርም ዘንድ ተዉኝ፤ ከቍ​ጣ​ዬም ልረፍ።

14 ሥጋ​ዬን በጥ​ርሴ እይ​ዛ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም በእጄ አጥ​ብቄ አኖ​ራ​ታ​ለሁ።

15 እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።

16 ዝንጉ ሰው በፊቱ አይ​ገ​ባ​ምና እርሱ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ን​ል​ኛል።

17 ነገ​ሬን ስሙ ስሙ፥ እኔ በጆ​ሮ​አ​ችሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለ​ሁና።

18 እነሆ፥ ወደ ፍርዴ ቀር​ቤ​አ​ለሁ። ጽድ​ቄም እን​ደ​ም​ት​ገ​ለጥ አው​ቃ​ለሁ።

19 አሁን ፈጽሜ ዝም እል ዘንድ፥ ከእኔ ጋር የሚ​ፋ​ረድ ማን ነው?

20 “ነገር ግን ሁለት ነገ​ርን ስጠኝ፤ የዚ​ያን ጊዜ ከፊ​ትህ አል​ሰ​ወ​ርም፤

21 እጅ​ህን ከእኔ አርቅ፤ ግር​ማ​ህም አታ​ስ​ደ​ን​ግ​ጠኝ።

22 ከዚ​ህም በኋላ ትጠ​ራ​ኛ​ለህ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ። ወይም አንተ ተና​ገር፥ አኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ።

23 ኀጢ​አ​ቶ​ችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስ​ታ​ው​ቀኝ።

24 “ፊት​ህን ከእኔ የሰ​ወ​ርህ፥ እንደ ጠላ​ት​ህም የቈ​ጠ​ር​ኸኝ ስለ​ምን ነው?

25 በነ​ፋስ እንደ ረገፈ ቅጠል ታፍ​ሰ​ኛ​ለ​ህን? ወይስ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዕብቅ ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለ​ህን?

26 ክፉ ነገ​ርን ጽፈ​ህ​ብ​ኛ​ልና፤ የል​ጅ​ነ​ቴ​ንም ኀጢ​አት ተቈ​ጣ​ጥ​ረህ አስ​ታ​ጥ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና።

27 እግ​ሮ​ች​ንም በድጥ አሰ​ነ​ካ​ከ​ልህ፥ ሥራ​ዬ​ንም ሁሉ መር​ም​ረ​ሃል፤ እግ​ሬም በቆ​መች ጊዜ ተው​ኸኝ።

28 እኔ እንደ አረጀ ረዋት፥ ብልም እን​ደ​ሚ​በ​ላው ልብስ ነኝ።

Siga-nos em:



Anúncios