Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ዘፀአት 38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት መሠ​ዊያ አሠ​ራር
( ዘፀ. 27፥1-8 )

1 ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ነበረ፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ነበረ።

2 ቀን​ዶ​ቹ​ንም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን አደ​ረ​ገ​በት፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በና​ስም ለበ​ጠው።

3 የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥ ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ሳት ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አደ​ረገ።

4 እንደ መረብ ሆኖም የተ​ሠራ የናስ መከታ ለመ​ሠ​ዊ​ያው አደ​ረገ፤ መከ​ታ​ውም እስከ መሠ​ዊ​ያው እኩ​ሌታ ይደ​ርስ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሚ​ዞ​ረው በደ​ረ​ጃው ታች አደ​ረ​ገው።

5 ለና​ሱም መከታ ለአ​ራቱ ማዕ​ዘን የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎች ስፍራ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለ​በ​ቶች አደ​ረገ።

6 መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ በና​ስም ለበ​ጣ​ቸው።

7 ይሸ​ከ​ሙ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው ጎን ባሉት ቀለ​በ​ቶች ውስጥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን አገባ፤ ከሳ​ን​ቃ​ዎ​ቹም ሠርቶ ክፍት አደ​ረ​ገው።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያው ሰን አሠ​ራር
( ዘፀ. 30፥18 )

8 የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ።


የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐደ​ባ​ባይ
( ዘፀ. 27፥9-19 )

9 ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ በኩል በስ​ተ​ቀኝ አደ​ባ​ባይ አደ​ረገ፤ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ጥሩ በፍታ የተ​ሠራ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ ነበረ።

10 ሃያ​ው​ንም ምሰ​ሶ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሃያ​ውን እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከናስ አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች ከብር አደ​ረገ።

11 በሰ​ሜ​ኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ከና​ስም የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና ሃያ እግ​ሮ​ችን፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ችም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ።

12 በም​ዕ​ራ​ብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም የናስ እግ​ሮች፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ።

13 በም​ሥ​ራ​ቅም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን አደ​ረገ።

14 በአ​ዜብ በኩል የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ነበሩ።

15 እን​ዲ​ሁም በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ሦስ​ትም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ሦስ​ትም እግ​ሮች ነበሩ።

16 በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሁሉ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ ተሠ​ር​ተው ነበር።

17 የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም እግ​ሮች የናስ፥ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ነበሩ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ጕል​ላ​ቶች በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ላሉ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ የብር ዘን​ጎች ነበ​ሩ​አ​ቸው።

18 የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ደጅ መጋ​ረጃ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ፥ ከጥ​ሩም በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ነበረ፤ ርዝ​መቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመ​ቱም እንደ አደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎች አም​ስት ክንድ ነበረ፤

19 ከናስ የተ​ሠሩ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ነበሩ፤ ኵላ​ቦ​ቹም የብር ነበሩ፤ ጕል​ላ​ቶ​ቹና ዘን​ጎ​ቹም በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር።

20 የድ​ን​ኳ​ኑም ካስ​ማ​ዎች፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ካስ​ማ​ዎች የናስ ነበሩ።


ለድ​ን​ኳኑ ሥራ የተ​ሰ​ጠው ወር​ቅና ብር

21 በካ​ህኑ በአ​ሮን ልጅ በይ​ታ​ምር እጅ የሌ​ዋ​ው​ያን ተል​እኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ታ​ዘዘ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥር​ዐት ይህ ነው።

22 ከይ​ሁዳ ነገ​ድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ አደ​ረገ።

23 ከእ​ር​ሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ነበረ፤ እር​ሱም በሰ​ማ​ያዊ፥ በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽ​መና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅ​ርጽ፥ የሽ​መ​ናና የጥ​ልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።

24 የተ​ሰ​ጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድ​ን​ኳኑ ሥራ ሁሉ የተ​ደ​ረ​ገው ወርቅ፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክ​ሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።

25 በማ​ኅ​በ​ሩም ከሚ​ቈ​ጠ​ሩት የተ​ገኘ ብር፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ መቶ መክ​ሊ​ትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ከሰባ አም​ስት ሰቅል ነበረ።

26 እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው አንድ አንድ ዲድ​ር​ክም አዋጣ፤ አንድ ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተ​ዋ​ጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ከተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።

27 መቶ​ውም የብር መክ​ሊት ለድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች እግ​ሮ​ችና ለመ​ጋ​ረ​ጃው ምሰ​ሶ​ዎች እግ​ሮች ተደ​ረገ፤ መቶ​ውም መክ​ሊት ለመቶ እግ​ሮች፤ ለአ​ንድ እግ​ርም አንድ መክ​ሊት ሆነ።

28 ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አም​ስት ሰቅል የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹን ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ጕል​ላ​ቶች ለበጠ።

29 የተ​ሰ​ጠ​ውም ናስ አራት መቶ ሰባ መክ​ሊ​ትና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።

30 ከእ​ር​ሱም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ደጃፍ እግ​ሮች፥ የና​ሱ​ንም መሠ​ዊያ፥ ለእ​ር​ሱም የሆ​ነ​ውን የና​ሱን መከታ፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥

31 በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ​ትን እግ​ሮች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ እግ​ሮች፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪ​ያም ያሉ​ትን ካስ​ማ​ዎች ሁሉ አደ​ረገ።

Siga-nos em:



Anúncios