Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ዘፀአት 20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዐሠ​ርቱ ትእ​ዛ​ዛት
( ዘዳ. 5፥1-21 )

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ሁሉ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦

2 “ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤

3 “ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ።

4 “በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ።

5 አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤

6 ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ አም​ላክ ነኝና።

7 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።

8 “የሰ​ን​በ​ትን ቀን ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አስብ።

9 ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ተግ​ባ​ር​ህ​ንም ሁሉ አድ​ርግ፤

10 ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ እን​ግዳ በእ​ር​ስዋ ምንም ሥራ አት​ሥሩ፤

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስ​ድ​ስት ቀን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ ፈጥሮ በሰ​ባ​ተ​ኛዋ ቀን ዐር​ፎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ን​በ​ትን ቀን ባር​ኮ​ታል፤ ቀድ​ሶ​ታ​ልም።

12 “አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።

13 “አት​ግ​ደል።

14 “አታ​መ​ን​ዝር።

15 “አት​ስ​ረቅ።

16 “በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር።

17 “የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ሚስት፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን ቤት አት​መኝ፤ እር​ሻ​ው​ንም፥ ሎሌ​ው​ንም፥ ገረ​ዱ​ንም፥ በሬ​ው​ንም፥ አህ​ያ​ው​ንም፥ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ ሁሉ ማን​ኛ​ው​ንም አት​መኝ።”


የሕ​ዝቡ መፍ​ራት
( ዘዳ. 5፥21-33 )

18 ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።

19 ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።

20 ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እን​ዳ​ት​ሠሩ እር​ሱን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ያድር ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና አት​ፍሩ” አላ​ቸው።

21 ሕዝ​ቡም ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​በት ወደ ጨለ​ማው ቀረበ።


መሠ​ዊ​ያ​ውን የሚ​መ​ለ​ከት ሕግ

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለያ​ዕ​ቆብ ቤት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲህ በል፦ እኔ ከሰ​ማይ እንደ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ እና​ንተ አይ​ታ​ች​ኋል።

23 የብር አማ​ል​ክ​ትን አታ​ም​ልኩ፤ የወ​ርቅ አማ​ል​ክ​ት​ንም አታ​ም​ልኩ። የዕ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አም​ላ​ክ​ንም አታ​ም​ልኩ፤ እን​ዲህ ያለ አም​ላ​ክን ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ።

24 ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።

25 የድ​ን​ጋ​ይም መሠ​ዊያ ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ ጠር​በህ አት​ሥ​ራው፤ በመ​ሣ​ሪያ ብት​ነ​ካው ታረ​ክ​ሰ​ዋ​ለ​ህና።

26 ኀፍ​ረተ ሥጋህ በእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ገ​ለጥ ወደ መሠ​ዊ​ያዬ በደ​ረጃ አት​ውጣ።

Siga-nos em:



Anúncios