Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


2 ዜና መዋዕል 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ገባ
( 1ነገ. 8፥1-9 )

1 ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።

2 በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አባ​ቶች ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በበ​ዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ተሰ​በ​ሰቡ።

4 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ሁሉ ታቦ​ቷን አነሡ።

5 የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አወጡ፤ ታቦ​ቷ​ንም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ አወጡ።

6 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በታ​ቦቷ ፊት ሆነው ከብ​ዛት የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር።

7 ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አም​ጥ​ተው በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች በነ​በ​ረው መቅ​ደስ አኖ​ሯት።

8 ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦ​ቷ​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በስ​ተ​ላዩ በኩል ይሸ​ፍኑ ነበር።

9 መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበ​ሩና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይ​ታ​ዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።

10 በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው ከሁ​ለቱ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።

11 ከመ​ቅ​ደ​ስም ከወጡ በኋላ በዚያ የነ​በ​ሩት ካህ​ናት ሁሉ ተቀ​ድ​ሰው ነበር፤ በሰ​ሞ​ና​ቸ​ውም አል​ተ​ከ​ፈ​ሉም ነበር።

12 መዘ​ም​ራ​ንም የነ​በ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ሁሉ፥ ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን፥ ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች ጋር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጥሩ በፍታ ለብ​ሰው ጸና​ጽ​ልና ከበሮ፥ መሰ​ን​ቆም እየ​መቱ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መቶ ሃያ ካህ​ናት መለ​ከት ይነፉ ነበር።

13 መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ መቆ​ምና ማገ​ል​ገል አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።

Siga-nos em:



Anúncios