Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


2 ዜና መዋዕል 27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኢ​ዮ​አ​ታም ዘመነ መን​ግ​ሥት
( 2ነገ. 15፥32-38 )

1 ኢዮ​አ​ታ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ትባል ነበር።

2 አባ​ቱም ዖዝ​ያን እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ አል​ገ​ባም፤ ሕዝ​ቡም ገና ይበ​ድል ነበር።

3 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የላ​ይ​ኛ​ውን በር ሠራ፤ በዖ​ፌ​ልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ።

4 በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በይ​ሁዳ ሀገር ላይ ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ በዱር ስፍ​ራ​ዎ​ችም አም​ባ​ዎ​ች​ንና ግን​ቦ​ችን ሠራ።

5 ከአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም። በዚ​ያም ዓመት የአ​ሞን ልጆች መቶ መክ​ሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ ግብር ሰጡት። እን​ዲ​ሁም ደግሞ የአ​ሞን ልጆ​ችና ንጉ​ሣ​ቸው በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውና በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት ሰጡት።

6 ኢዮ​አ​ታ​ምም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​አ​ልና በረታ።

7 የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገ​ሮች፥ ሰል​ፉም ሁሉ፥ ሥራ​ውም፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።

8 መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።

9 ኢዮ​አ​ታ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

Siga-nos em:



Anúncios