Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


2 ዜና መዋዕል 16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል እንደ ተዋጉ
( 1ነገ. 15፥17-22 )

1 አሳ በነ​ገሠ በሠ​ላሳ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በይ​ሁዳ ላይ ዘመተ፥ ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ አሳ ማንም መው​ጣ​ትና መግ​ባት እን​ዳ​ይ​ችል ራማን ሠራት።

2 አሳም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ከን​ጉሥ ቤት መዝ​ገብ ብርና ወርቅ ወስዶ፦ በደ​ማ​ስቆ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ሶርያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር ላከ። እን​ዲ​ህም አለው፦

3 “በአ​ባ​ቴና በአ​ባ​ትህ መካ​ከል እንደ ነበ​ረው ቃል ኪዳን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አድ​ርግ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ርቅ መጥ​ተህ ትወ​ጋው ዘንድ እነሆ፥ ወር​ቅና ብር ልኬ​ል​ሃ​ለሁ።”

4 ወልደ አዴ​ርም ንጉ​ሡን አሳን ሰማው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰደደ፤ እነ​ር​ሱም አእ​ዮ​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ማ​ይ​ም​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም አው​ራጃ ከተ​ሞች ሁሉ መቱ።

5 ባኦ​ስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥ​ራት ተወ፤ ሥራ​ው​ንም አቋ​ረጠ።

6 የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ባኦስ ይሠ​ራ​በት የነ​በ​ረ​ውን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ እር​ሱም ገባ​ዖ​ን​ንና መሴ​ፋን ሠራ​በት።

7 በዚ​ያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “በሶ​ርያ ንጉሥ ታም​ነ​ሃ​ልና፥ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​መ​ን​ህ​ምና ስለ​ዚህ የሶ​ርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእ​ጆ​ችህ አም​ል​ጠ​ዋል።

8 ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”

10 አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።

11 የአ​ሳም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።

12 አሳም በነ​ገሠ በሠ​ላሳ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት እግ​ሩን ታመመ፤ ደዌ​ውም ጸና​በት፤ ነገር ግን በሕ​ማሙ ጊዜ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ገም።

13 አሳም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በነ​ገ​ሠም በአ​ርባ አን​ደ​ኛው ዓመት ሞተ።

14 ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።

Siga-nos em:



Anúncios