1 ዜና መዋዕል 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የይሳኮርም ልጆች፤ ቶላ፥ ፋዋ፥ ያሱብ፥ ሰምሮን፥ አራት ናቸው። 2 የቶላም ልጆች፤ ኦዚ፥ ረፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሰሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ። 3 የኦዚም ልጆች ይዝረሕያ፤ የይዝረሕያም ልጆች ሚካኤል፥ አብድዩ፥ ኢዩኤል፥ ይሴያ አምስት ናቸው፤ ሁሉም አለቆች ነበሩ። 4 ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤት ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። 5 ወንድሞቻቸውም በይሳኮር ወገኖች ሁሉ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች በትውልዳቸው ሁሉ የተቈጠሩ ሰማንያ ሰባት ሺህ ነበሩ። 6 የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይድኤል ሦስት ነበሩ። 7 የቤላም ልጆች፥ ኤሲቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሬሙት፥ ዔሪ አምስት ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ። 8 የቤኬርም ልጆች ዝሜራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮኤናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ ዓብያ፥ ዓናቶት፤ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ። 9 በየትውልዳቸውም መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 10 የይዴኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኬሳአር ነበሩ። 11 እነዚህ ሁሉ የይዴኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 12 ደግሞም ሳፊን፥ ሑፊም የዔር ልጆች፥ ሑሲም የአሔር ልጅ ነበረ። 13 የንፍታሌምም ልጆች፥ ያሕጽኤል፥ ጎኒ፥ ዬጽር፥ ሼሌም፥ እነዚህ አራቱ የባላ ልጆች ነበሩ። 14 የምናሴ ልጆች ሶሪያዪቱ ቁባቱ የወለደችለት አስርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው። 15 ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትየዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰዓድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት። 16 የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው፤ የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። 17 የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ። 18 እኅቱ መለኪት ኢሱድን፥ አቢዔዜርን፥ መሕላን ወለደች። 19 የሰሜራም ልጆች አሒያን፥ ሴኬም፥ ሌቅሔ፥ አኔዓም ነበሩ። 20 የኤፍሬም ልጆች፤ ሱቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታክት፤ 21 ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ ልጁ ኤድር፥ ልጁ ኤልዓድ ነበሩ፤ የሀገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና ገደሉአቸው። 22 አባታቸው ኤፍሬምም ብዙ ቀን አለቀሰ፤ ወንድሞቹም ሊያጽናኑት መጡ። 23 ወደ ሚስቱም ገባ፥ አረገዘችም፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤቴም መከራ ሆኖአልና ሲል ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው። 24 የሴት ልጁም ስም ሲአራ ነበረ፤ በዚያም በቀሩት ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንን ሠራ የኡዛንም ልጁ ሠይራ ነበረ፤ 25 ወንዶች ልጆቹም ራፋኢ፥ ሳራፍ፥ ልጁ ቴላ፥ ልጁ ታሐን፤ 26 ልጁ ለአዳን፥ ልጁ ዓሜሁድ፥ ልጁ ኤሌሳማ፤ 27 ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ። 28 ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞም ሴኬምና መንደሮችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፤ 29 በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ በላድና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ ያዕቆብ የተባለ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ። 30 የአሴር ልጆች፤ ኢያምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሬዓ፥ እኅታቸውም ሤራሕ ነበሩ። 31 የበሪዓም ልጆች፤ ሔቤርና፥ የቤርዛዊት አባት የነበረው መልኪኤል ናቸው። 32 ሔቤርም ያፍሌጥን፥ ሳሜርን፥ ኮታምን፥ እኅታቸውንም ሶላን ወለደ። 33 የያፍሌጥም ልጆች፤ ፋሴክ፥ ቢምሃል፥ ዓሴት ነበሩ፤ እነዚህ የያፍሌጥ ልጆች ነበሩ። 34 የሳሜርም ልጆች፤ አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሁባ፥ አራም ነበሩ። 35 የወንድሙም የኡላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ። 36 የጾፋም ልጆች፤ ሴዋ፥ ሐርኔፍር፥ ሦአል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ 37 ቤጼር፥ ሆድ፦ ሳማ፦ ሰሌሳ፥ ይትራን፦ ብኤራ ነበሩ። 38 የዬቴርም ልጆች፤ ያፊና፥ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ። 39 የዑላ ልጆች፤ ኤራ፥ ሐኔኤል፥ ሪጽያ ነበሩ። 40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በሰልፍ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ። |