1 ዜና መዋዕል 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የሌዊ ትውልድ 1 የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ። 2 የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። 3 የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። 4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስም አቢሱን ወለደ፤ 5 አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤ 6 ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤ 7 መራዮትም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 8 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማኦስን ወለደ፤ 9 አኪማኦስም ዓዛርያን ወለደ፤ አዛርያም ዮሐናንን ወለደ፤ 10 ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤ 11 ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሳሎምን ወለደ፤ 13 ሳሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤ 14 ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15 ኢዮሴዴቅም፥ ይሁዳና ኢየሩሳሌም በናቡከደነፆር እጅ በተማረኩ ጊዜ ተማርኮ ሄደ። 16 የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 17 የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ፥ ሰሜኢ። 18 የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 19 የሜራሪም ልጆች፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ፥ የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። 20 ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፤ 21 ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ። 22 የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፤ 23 ልጁ ሕልቃና፥ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፤ 24 ልጁ ተአት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል። 25 የሕልቃናም ልጆች፤ አማሤ፥ አኪሞት። 26 ልጁ ሕልቃና፤ ልጁ ሱፌ፤ ልጁ ናሔት፤ 27 ልጁ ኤልያብ፤ ልጁ ኢያሬምያል፤ ልጁ ሕልቃና፤ ልጁ ሳሙኤል። 28 የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ። 29 የሜራሪ ልጆች፤ ሞሓሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ዖዛ፥ 30 ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ። 31 ዳዊትም ታቦቷ በምታርፍበት ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። 32 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር። 33 አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ነበሩ፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዩኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፤ 34 የሕልቃና ልጅ፥ የይሮዓም ልጅ፥ የኤላኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፤ 35 የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥ የአማሤ ልጅ፤ 36 የሕልቃና ልጅ፥ የኢዩኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፤ 37 የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ 38 የይሰአር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው። 39 በቀኙም የሚቆመው ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፤ 40 የሚካኤል ልጅ፤ የበዓሣያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፤ 41 የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፤ 42 የኤታን ልጅ፥ የዛማ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፤ 43 የኢያኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው። 44 በግራቸውም በኩል የሚቆሙ ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቄሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፤ 45 የአሳቢ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ፤ 46 የአማሴ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፤ 47 የሞአሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ። 48 ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን እንደ እየባቶቻቸው ቤቶች ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ። 49 አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። 50 የአሮንም ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፤ 51 ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፤ 52 ልጁ መራዮት፥ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ 53 ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማኦስ። 54 ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። 55 ለእነርሱ በይሁዳ ሀገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋም ዙሪያ የነበረውን መሰማሪያ ሰጡ፤ 56 የከተማዪቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ። 57 ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ። 58 የኢያቴርን ከተማና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፤ 59 ዓሳንንና መሰማሪያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማሪያዋን፤ 60 ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። 61 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 62 ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። 63 ለሜራሪም ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 64 የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ሰጡ። 65 ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ። 66 ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። 67 በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ደግሞም ጋዜርንና መሰማሪያዋን፤ 68 ዮቅምዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ 69 ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን ሰጡአቸው። 70 ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቤልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ። 71 ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጋውሎንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ፤ 72 ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ዳብራትና መሰማሪያዋ፤ 73 ራሞትና መሰማሪያዋ፥ ዓኔምና መሰማሪያዋ፤ 74 ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማሪያዋ፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋ፤ 75 ሐቆቅና መሰማሪያዋ፥ ረዓብና መሰማሪያዋ፤ 76 ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ። 77 ለቀሩትም ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰማሪያዋ፥ ታቦርና መሰማሪያዋ፤ 78 ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሶንና መሰማሪያዋ፤ 79 ቅዴሞትና መሰማሪያዋ፥ ሜፍዓትና መሰማሪያዋ፤ 80 ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰማሪያዋ፥ መሃናይምና መሰማሪያዋ፤ 81 ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጡ። |