Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


1 ዜና መዋዕል 18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዳዊት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ የተ​ቀ​ዳ​ጀው ድል
( 2ሳሙ. 8፥1-18 )

1 ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ ጌት​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።

2 ሞዓ​ብ​ንም መታ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።

3 ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።

4 ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ አንድ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞች ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ለመቶ ሰረ​ገ​ሎች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ብቻ አስ​ቀ​ርቶ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን ፈረ​ሶች ቋንጃ ቈረጠ።

5 ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።

6 ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።

7 ዳዊ​ትም ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ ማር​ዳ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይዞ​አ​ቸው መጣ።

8 ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።

9 የኤ​ማ​ትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን፥ ጭፍ​ራ​ው​ንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ።

10 ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።

11 ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።

12 ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ከኤ​ዶ​ማ​ው​ያን በጨው ሸለቆ ውስጥ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች ገደለ።

13 በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።

14 ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።

15 የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሔ​ሉ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።

16 የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶ​ቅና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ አቤ​ሜ​ሌክ ካህ​ናት ነበሩ፤ ሱሳ ጸሓፊ ነበረ።

17 የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ ሹም ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጆች በን​ጉሡ አጠ​ገብ አለ​ቆች ነበሩ።

Siga-nos em:



Anúncios