1 ዜና መዋዕል 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ከአዳም እስከ አብርሃም ያለው ሐረገ ትውልድ ( ዘፍ. 5፥1-32 ፤ 10፥1-32 ፤ 11፥10-26 ) 1 አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ 2 ቃይናን፥ መላልኤል፥ ያሬድ፥ 3 ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥ 4 ኖኅ፥ ልጆቹም ሴም፥ ካም፥ ያፌት። 5 የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ይሕያን፥ ኤልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕና ቲራም። 6 የጋሜርም ልጆች አስካናስ፥ ሪፋት፥ ቶርጋማ። 7 የይሕያ ልጆች ኤልሳ፥ ተርሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ። 8 የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምስራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን። 9 የኩሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሳበታ፥ ሬግማን፥ ሱቦን። የሬግማንም ልጆች፤ ሴባ፥ ዳዳን። 10 ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ አዳኝና ኀያል መሆንን ጀመረ። 11 ምሥራይም ሎዲአምን፥ ዐናኒምን፥ ሎቢንን፥ ንፍታሌምን፥ 12 ጴጥሮሳኒኤምን፥ ፍልስጥኤማውያን የወጡበትን ከሰሎንኤምን፥ ከፋቱሪምን ወለደ። 13 ከነዓን የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጤዎንን፥ 14 ኤያቡሴዎንን፥ አሞሬዎንን፥ ጌርጌሴዎንን፥ 15 አዌዎንን፥ አረቄዎንን፥ ኤሴነዎንን፥ 16 አራዴዎንን፥ ሰማሬዎንን፥ አማቲን ወለደ። 17 የሴምም ልጆች፤ አይላም፥ አሡር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ የአራምም ልጆች፤ ኡስ፥ ዑል፥ ጋቴር፥ ሞሳክ። 18 አርፋክስድም ቃይናንን ወለደ፤ ቃይናንም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ። 19 ለኤቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፋፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ፤ 20 ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍን፥ ኤራሞትን፥ ያራሕን፥ 21 ቄዱራምን፥ ኤዜልን፥ ዲቅላምን፥ 22 ጌማሄልን፥ ኤልሜሄልን፥ ሳባን፥ 23 ኦፌርን፥ ሄውላን፥ ኦራምን፥ ዑካብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። 24 የሴምም ልጆች፤ አይላም፥ አሡር፥ አርፋክስድ፥ ሳላን፥ ቃይናን፥ 25 ዔቦር፥ ፋሌቅ፥ ራግው፥ 26 ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ 27 አብርሃም የተባለው አብራም። የይስማኤል ሐረገ ትውልድ ( ዘፍ. 25፥12-16 ) 28 የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅ፥ ይስማኤል። 29 ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የይስማኤል በኵር ልጅ ናቢዎት፤ ቄዳር፥ ቢዲሄል፥ ሙባሳን፥ 30 ሚስማዕ፥ ይዱማ፥ ማሴ፥ ኬዲድ፥ ቴማን፤ 31 የጡር፥ ናፌስ፥ ቂዳማ፤ እነዚህ የይስማኤል ልጆች ናቸው። 32 የአብርሃም ዕቅብት ኬጡራ የወለደችለት ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳም፥ ምድያን፥ ዮሳብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን። 33 የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖሕ፥ አቢዳን፥ ኤልዳን። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ። የኤሳው ሐረገ ትውልድ ( ዘፍ. 36፥1-9 ) 34 አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና ያዕቆብ ነበሩ። 35 የዔሳው ልጆች፤ ዔልፋዝ፥ ራጉኤል፥ ይዑል፥ ይጉሎም፥ ቆሬ። 36 የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴምናስ፥ አማሌቅ። 37 የራጉኤል ልጆች፤ ናቦት፥ ዛራ፥ ሴዴት፥ ሞዛ። 38 የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሳባን፥ ሴቤጎን፥ ዓናን፥ ዴሶን፥ አሦር፥ ዴሳን። 39 የሎጣንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ኤማን፤ ታምናን የሎጣን እኅት ነበረች። 40 የሦባል ልጆች፤ ጎለም፥ ማኔሐት፥ ኔባል፥ ሳፍር፥ አናን፤ የሴቤጎን ልጆች፤ ሐያን፥ አናም፤ 41 የአናም ልጆች፤ ዴሶን፥ የአናም ሴት ልጅ ኤሌማ፥ የዴሶንም ልጆች፤ አምዳን፥ ኤስቦን፥ ኢይትራን፥ ካራን፥ እሊህ ናቸው። 42 የአሦር ልጆች፤ በለዓን፥ ዛዕዋን፥ ኢይዓቃን። የዴሶን ልጆች፤ ዖስ፥ አራን። የኤዶም ነገሥታት ( ዘፍ. 36፥32-43 ) 43 በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲናባ ነበረ። 44 ባላቅም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። 45 ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የቴማን ሀገር ሰው አሶም ነገሠ፤ 46 አሶምም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ በሞዓብ ሜዳ ምድያምን የመታው የባራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ጌቴም ነበረ። 47 አዳድም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የማስቃ ሰው ስማዓ ነገሠ። 48 ስማዓም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ በወንዙ አጠገብ ያለችው የረኆቦት ሰው ሳኦል ነገሠ። 49 ሳኦልም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የአክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ። 50 የአክቦር ልጅ በኣልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የባራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፌጎር ነበረ፤ ሚስቱም የሚዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች። 51 አዳድም ሞተ፤ የኤዶምያስም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቴምናዕ አለቃ፥ ጎለም አለቃ፥ የቴት አለቃ፥ 52 አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፌኖን አለቃ፥ 53 ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ መብሳር አለቃ፥ 54 መግዴኤል አለቃ፥ ዛፎአል አለቃ፤ እነዚህ የኤዶምያስ አለቆች ነበሩ። |