Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


መዝሙር 150 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 150

1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።

2 ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና አመስግኑት።

3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።

4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት።

5 ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት።

6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
Siga-nos em:



Anúncios