Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


መዝሙር 108 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 108
108፥6-13 ተጓ ምብ – መዝ 60፥5-12
የዳዊት መዝሙር፤ ማሕሌት።

1 አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ።

2 በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

3 ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ።

4 ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች።

5 አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።

6 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም።

7 እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

8 ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።

9 ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”

10 ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል?

11 እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም።

12 በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።

13 በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
Siga-nos em:



Anúncios