Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


መዝሙር 150 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔርን አመስግኑ!

1 እግዚአብሔርን አመስግኑ! እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት! የሚያስደንቅ ኀይሉ ባለበት በሰማይ አመስግኑት!

2 ስላደረገው ድንቅ ሥራ አመስግኑት፤ ወደር ስለማይገኝለት ታላቅነቱ አመስግኑት።

3 በመለከት አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።

4 በከበሮና በማሸብሸብ አመስግኑት፤ በክራርና በዋሽንት አመስግኑት።

5 በጸናጽል ድምፅ አመስግኑት፤ ከፍተኛ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።

6 ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት! እግዚአብሔር ይመስገን!

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Siga-nos em:



Anúncios