Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


መዝሙር 121 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር ጠባቂአችን መሆኑ

1 እኔ ወደ ተራራዎች እመለከታለሁ፤ ታዲያ፥ ርዳታ የማገኘው ከወዴት ነው?

2 ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።

3 ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።

4 የእስራኤል ጠባቂ ከቶ አያንቀላፋም፤ ፈጽሞም አይተኛም።

5 እግዚአብሔር ጠባቂህ ነው፤ በቀኝህም ሆኖ ያጠላልሃል።

6 ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አያደርሱብህም።

7 እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ሕይወትህንም በሰላም ይጠብቃል።

8 ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Siga-nos em:



Anúncios