Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -


ሕዝቅኤል 15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ጥቅም የሌለው የወይን ተክል

1 የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለው የወይን ቅርንጫፍ፥ ከሁሉም ዛፎች ይልቅ የወይን ግንድ የሚበልጠው እንዴት ነው?

3 ማንኛውም ሥራ ለመስራት እንጨት ከእርሱ ይወስዳል? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኩላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?

4 እነሆ ለመቃጠል ለእሳት ተስጥቷል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶታል፥ መካከሉም ተቃጥሏል፥ ለሥራ ይጠቅማልን?

5 እነሆ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላውና ከተቃጠለ በኋላ ሥራ ይሠራበታልን?

6 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት እንዲበላው እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።

7 ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

8 እምነተ ቢስ ሆነዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

Siga-nos em:



Anúncios