Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ጥበብ 11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ጥበብ የእስራኤልን ሕዝብ በበርሃ እንደ መራቻቸው 1 እርስዋ በቅዱሱ ነቢይ እጅ ሥራቸውን አቃናች፤ 2 ማንም ወዳልኖረበት ምድረ በዳም ሄደው ኖሩ። ባልተረገጠች ቦታም የድንኳኖቻቸውን ካስማ ተከሉ። 3 ተዋጊዎችንም ተቋቋሟቸው፤ ጠላቶችንም ተበቀሏቸው። 4 በተጠሙ ጊዜም ጠሩህ፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃ ተሰጣቸው። ከጽኑ ድንጋይም ለጥማቸው ፈውስ ተሰጣቸው። 5 ጠላቶቻቸውም በዚህ ሥራ ተፈርዶባቸው ጠፉ። 6 በዚህም ተቸግረው በተጨነቁ ጊዜ በጎ ነገርን አደረግህላቸው። 7 በተገደሉት ሰዎች ደም እነዚያ ባደፈረሱት በማይጐድለው ወንዝ ምንጭ ፋንታ፥ 8 ሕፃናት በዐዋጅ መገደላቸውን ለመዝለፍ በተስፋ ሳታስጠብቅ ፈጥነህ ያመነጨኸውን ብዙ ውኃ ሰጠኻቸው። 9 እንደዚሁም በተጠሙ ጊዜ ስለተፈታተኑህ ተቃዋሚዎችን ፈረድህባቸው። 10 እነርሱ ግን በምሕረትህ ተገሠጹ፥ ክፉዎችም በመዓት በተፈረደባቸው ጊዜ እንዴት እንደ ተቀጡ ዐወቁ። 11 እነዚህንም እንደሚቀጣ አባት ገሠጽኻቸው። እነዚያን ግን ርኅራኄ እንደሌለው ንጉሥ ተከትለህ ቀጣኻቸው። 12 በዚህም አምሳል ገረፍኻቸው። ሳሉም፥ ሳይኖሩም አሳዘንኻቸው። 13 እጥፍ ኀዘን አግኝቶአቸዋልና፥ ያለፈውንም ክፉ ነገር የማሰብ ጩኸት አግኝትዋቸዋልና። 14 በመከራቸውም በጎ ነገር እንዳደረገላቸው በሰሙ ጊዜ እነርሱ ከእግዚአብሔር የተገኘ ደስታ አደረጉት። በኃጥኣን ላይ የሚደርስ ቅጣት 15 ዳግመኛም በክፋት ቀድሞ የጣሉትን አጡት፤ ከዚህም በኋላ በመዘባበት ከእርሱ ሸሹ፤ ከትእዛዙ መውጣት ፍጻሜ የተነሣም አደነቁ፥ ጻድቃንም እንደ ተጠሙ እነርሱ የተጠሙ አይደሉም። 16 አእምሮ በሌላት በልቡናቸው ክፋት በሳቱባት ጊዜ፥ የማይናገር፥ የተናቀና ከንቱ ሀብት እንስሳን አምልከዋልና፥ 17 ሰው በበደለበት ሥራ እንዲፈረድበት ያውቁ ዘንድ ለመበቀል የማይናገር ብዙ እንስሳን ላክህባቸው። 18 ዓለምን ካለመኖር ለፈጠረ ሁሉን ለሚችል ቀኝ እጅህ ብዙ ድቦችንና ቍጡ አንበሶችን ትልክባቸው ዘንድ አይሳነውምና። 19 ያም ባይሆን ድንገት የተፈጠሩ የማይታወቁ፥ የሚያላልብና የሚፋጅ እሳትን የሚተነፍሱ፥ ያም ባይሆን የሚከረፋ የጢስ መዓዛን የሚተነፍሱ፥ ያም ባይሆን ከክፉ ዓይናቸው የእሳት ፍንጣሪን ቦግ ቦግ የሚያደርጉ ቍጣን የተሞሉ አውሬዎችን ላክህባቸው። 20 ሊያጠፋቸው የሚችል ክፋታቸው ወይም ፍርዳቸው ብቻ አይደለም። ነገር ግን መልካቸው ባስፈራቸውና ባጠፋቸው ነበር። እግዚአብሔር ኀያል መሓሪም ስለ መሆኑ 21 ከዚህም በቀር፦ ስታባርራቸው፥ በኀይልህ መንፈስም ስታጠፋቸው፥ በአንዲት ምልክት ይጠፉ ዘንድ በተገባቸው ነበር። ነገር ግን ሁሉን በመጠን፥ በቍጥርና በሚዛን ሠራህ። 22 የከሃሊነትህ ገናናነት በአንተ ዘንድ ሁልጊዜ ይኖራልና፥ የክንድህ ጽንዐት ኀይልንም ማን ይቃወማታል? 23 ዓለሙ ሁሉ በፊትህ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነውና፥ በማለዳም በምድር ላይ እንደ ወረደች እንደ ጠል ጠብታ ነውና። 24 አንተ ሁሉን የምትችል ነህና ሁሉን ይቅር ትላለህ፥ ለንስሓም እየጠበቅኸው የሰውን ኀጢአት ቸል ትላለህ። 25 ያሉትን ሁሉ ትወዳለህ፥ ከፈጠርኸው ፍጥረትም ምንም የምትንቀው የለም፥ ብትጠላውስ ኖሮ አትፈጥረውም ነበርና። 26 አንተ ካልወደድኸው በፊትህ እንደምን በጸና ነበር! አንተስ ካልጠራኸው እንደምን በተጠበቀ ነበር! 27 ለፍጥረቱም ሁሉ ትራራለህ፥ ይቅርም ትላለህ። ሰውን የምትወድድ አቤቱ፥ ሁሉ ያንተ ነውና፥ |