Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ሲራክ 48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ነቢዩ ኤልያስ 1 ነቢዩ ኤልያስም እንደ እሳት ተነሣ፥ ቃሉም እንደ ነበልባል ያቃጥል ነበር። 2 ረኃብንም አመጣባቸው፤ በቅንዓቱም አሳነሳቸው። 3 በእግዚአብሔርም ቃል ሰማይን ዘጋው፤ ከሰማይም እሳትን ሦስት ጊዜ አወረደ። 4 ኤልያስ ሆይ፥ በተአምራትህ እንዴት ከበርህ! እንዳንተስ የተመካ ማንነው? 5 በልዑል ቃል ከሞቱ ሰዎች ለይቶ ምውትን ከመቃብር ያስነሣ ማንነው? 6 ነገሥታቱን ወደ ሞት፥ የከበሩ ሰዎቹንም ከአልጋቸው ያወረዳቸው ማንነው? 7 በሲና የእግዚአብሔርን ተግሣጽ፥ በኮሬብም የበቀልን ፍርድ የሰማ ማንነው? 8 ይበቀሉ ዘንድ ነገሥታቱን፥ ከእርሱም ቀጥሎ ይተኩ ዘንድ ነቢያትን የቀባቸው ማንነው? 9 በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ወደ ሰማይ የወጣ ማንነው? 10 መቅሠፍቱ ከመውረዱ አስቀድሞ የእግዚአብሔርን ቍጣ ይመልስ ዘንድ፥ የአባትንም ልብ ወደ ልጅ ይመልስ ዘንድ፤ የያዕቆብንም ወገኖች ያጸናቸው ዘንድ በተወሰነ ዘመን የተጻፈለት ማንነው? 11 የሚያውቁህና በፍቅርህ ያጌጡ ሰዎች ብፁዓን ናቸው፥ እኛም ስለ አንተ በሕይወት እንኖራለን። ነቢዩ ኤልሳዕ 12 በእሳት ሠረገላ ወደ ላይ የወጣ ኤልያስ ነው፤ ከእርሱም መንፈስ የተመላ ኤልሳዕ ነበረ፤ በዘመኑም አለቆች አላስደነገጡትም፤ ማንም እርሱን የተቋቋመው አልነበረም። 13 ከነገሩም ሁሉ የተሳነው አልነበረም፤ ከሞተም በኋላ በድኑ ትንቢትን ተናገረ። 14 በሕይወቱም ሳለ ድንቅ ተአምራትን አደረገ፤ በሞቱም ሥራው ድንቅ ነበረ። 15 ከዚህም ሁሉ ጋር ሕዝቡ ንስሓ አልገቡም፤ ከሀገራቸውም ተማርከው እስኪሄዱ ድረስ ኀጢአታቸውን አልተዉም፤ በሀገሩም ሁሉ ተበተኑ፤ ከሕዝቡም ጥቂት ሰዎች ቀሩ፤ ገዢም ከዳዊት ቤት ቀረ። 16 ከእነርሱም ደግ ሥራ የሠሩ ነበሩ፤ ኀጢአትንም ያበዟት ነበሩ። ንጉሡ ሕዝቅያስ 17 ሕዝቅያስም ከተማውን አጸና በመካከልዋም ውኃን አስገባ፤ ዓለቱንም በብረት ቈፈረ፤ የውኃ መስኖ አሠራ። 18 ሰናክሬምም በዘመኑ ዘመተ፤ ራፋስቂስንም ላከው፤ ወደ እርሱም ሄዶ በጽዮን ላይ እጁን አነሣ፤ ታበየ፤ አፉንም ከፍ ከፍ አድርጎ ተናገረ። 19 ያን ጊዜም ልቡናቸው ደነገጠባቸው፤ እጃቸውም ዛለ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ያዛቸው። 20 ይቅር ባይ እግዚአብሔርንም ለመኑት፤ እጃቸውንም ወደ እርሱ አነሡ፤ ቅዱሱም ከሰማይ ፈጥኖ ሰማቸው፤ በኢሳይያስም እጅ አዳናቸው። 21 የአሦርንም ሠራዊት አጠፋ፤ መልአኩም አጠፋቸው። 22 ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ሥራ ሠርትዋልና፤ በራእዩ ታላቅና ታማኝ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስም እንዳዘዘው የአባቱ የዳዊትን መንገድ አጽንትዋልና። 23 ፀሐይም በዘመኑ ከመሄድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ ለንጉሡም ዘመን ጨመረለት። 24 በታላቅ መንፈስም በመጨረሻ የሚሆነውን አየ፤ በጽዮን የሚያለቅሱትንም አጽናናቸው። 25 ለዘለዓለሙ የሚሆነውን፥ የተሰወረውንም ሳይሆን ተናገረ። |