Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጥበ​ብስ በቀ​ደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመ​ረ​መ​ረች።

2 በሃ​ይ​ማ​ኖት ስማ​ቸ​ውን ላስ​ጠሩ ሰዎች ትን​ቢ​ትን ታስ​ተ​ም​ራ​ለች፤ ወደ ነቢ​ያ​ትም ምሳሌ ታገ​ባ​ለች።

3 የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ምሳሌ ትመ​ረ​ም​ራ​ለች፤ ምሳ​ሌ​ው​ንም ወደ መተ​ር​ጐም ትመ​ል​ሳ​ለች።

4 በመ​ኳ​ን​ን​ትም መካ​ከል ትጠ​ቅ​ማ​ለች፤ በአ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ትታ​ያ​ለች፤ ልዩ ወደ ሆኑ ወደ አሕ​ዛ​ብም ሀገር ትገ​ባ​ለች፤

5 ሰዎ​ችን በበ​ጎም፥ በክ​ፉም ትፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለ​ችና፥ ወደ ፈጣ​ሪው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሄድ ዘንድ፥ በል​ዑ​ልም ፊት ይጸ​ልይ ዘንድ ልቡን ይመ​ል​ሳል፤ አፉ​ንም ይከ​ፍ​ታል፤ ይለ​ም​ና​ልም፤ ስለ ኀጢ​አ​ቱም ይና​ዘ​ዛል።

6 ነገር ግን ገናና የሆ​ነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፈ​ቀደ፥ የጥ​በ​ብ​ንም መን​ፈስ ካሳ​ደ​ረ​በት፥ እርሱ የጥ​በ​ቡን ነገር ያፈ​ል​ቃል፤ በጸ​ሎ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛል።

7 እር​ሱም ጥበ​ብ​ንና ምክ​ርን ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል፤ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ያውቅ ዘንድ ያሳ​ስ​በ​ዋል።

8 እር​ሱም የት​ም​ህ​ር​ቱን ጥበብ ያሳ​ያል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኪ​ዳን ሕግም ይመ​ካል።

9 ስለ ጥበ​ቡም ብዙ ሰዎች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም አይ​ደ​መ​ሰ​ስም፤ ስም አጠ​ራ​ሩም አይ​ጠ​ፋም፤ ስሙም ለልጅ ልጅ ጸንቶ ይኖ​ራል።

10 አሕ​ዛ​ብም ጥበ​ቡን ይና​ገ​ራሉ፤ በሸ​ንጎ መካ​ከ​ልም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

11 ከሺህ ልጅ ስምን ማስ​ጠ​ራት ይሻ​ላል፤ ከሞ​ተም በኋላ ሥራው ጸንቶ ይኖ​ራል።


የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር

12 ዳግ​መ​ኛም አስቤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እንደ ሙሉ ጨረቃ ሙሉ ነኝና።

13 የጻ​ድ​ቃን ልጆች ስሙኝ፤ ለም​ልሙ፤ ታደሱ፤ አበባ በም​ድረ በዳ ጠል እን​ደ​ሚ​ያ​ብብ አብቡ።

14 እንደ ሊባ​ኖስ መዓዛ መዓ​ዛ​ችሁ ይጣ​ፍጥ፤ አበ​ባ​ች​ሁን እንደ ጽጌ​ረዳ አብ​ቅሉ ፤ መዓ​ዛ​ች​ሁ​ንም አጣ​ፍጡ፤ መዝ​ሙ​ርን ዘምሩ፤ በሥ​ራ​ውም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።

15 ስሙን አግ​ን​ኑት፤ በአ​ንድ ሺህ መዝ​ሙ​ርና በመ​ሰ​ንቆ ስሙን አግ​ን​ኑት በም​ታ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትም ጊዜ እን​ዲህ በሉ።

16 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ገናና ነው። እጅ​ግም ያማረ ነው፤ ሥር​ዐ​ቱም ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ነው።”

17 “ይህ ለም​ን​ድን ነው? ያስ ለም​ን​ድን ነው?” ማለት አይ​ገ​ባም፤ ሁሉም በጊ​ዜው ይፈ​ቀ​ዳል፤ ውኃ​ው​ንም በቃሉ እንደ ግድ​ግዳ አጸ​ናው፤ በአፉ ቃልም እንደ ኵሬ ውኃ፤

18 በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ የተ​ወ​ደደ ነው፤ መድ​ኀ​ኒ​ት​ነ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጐ​ድል የለም።

19 የሰው ሁሉ ሥራ በፊቱ ነው፤ ከዐ​ይ​ኖ​ቹም ፊት መሰ​ወር የሚ​ችል የለም።

20 ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ሁሉን ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ምንም ልዩ ፍጥ​ረት የለም።

21 ሁሉም ለመ​ፍ​ቅ​ዳ​ቸው ተፈ​ጥ​ሯ​ልና “ይህ ለም​ን​ድን ነው? ያስ ለም​ን​ድን ነው?” የሚል የለም።

22 በረ​ከ​ቱም እንደ ፈሳሽ ውኃ መላች፤ እንደ ጎርፍ ውኃም ምድ​ርን አረ​ካ​ቻት፤

23 እን​ደ​ዚሁ ቍጣው አሕ​ዛ​ብን ከፈ​ለ​ቻ​ቸው።

24 የጻ​ድቅ መን​ገዱ የቀና ነው፤ የኃ​ጥእ መን​ገድ ግን ዕን​ቅ​ፋት ነው፤ ውኃ​ው​ንም የሚ​ለ​ው​ጠው፥ ጨውም የሚ​ያ​ደ​ር​ገው እርሱ ነው።

25 በጎ ነገር ከጥ​ንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈ​ጠ​ረች፤ እን​ደ​ዚሁ ክፉ ነገ​ርም ለኃ​ጢ​አ​ተ​ኞች ተፈ​ጠ​ረች።

26 የሰው የመ​ፍ​ቅዱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ፥ ውኃ፥ እሳት፥ ብረት፥ ጨው፥ እህል፥ ስንዴ፥ ማር፥ ወተት፥ ወይን፥ ዘይ​ትና ልብስ ነው።

27 ይህ ሁሉ ለጻ​ድ​ቃን ሰዎች በረ​ከ​ታ​ቸው ነው፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ወደ ክፉ ይመ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ዋል።

28 ለበ​ቀል የተ​ፈ​ጠ​ረች መን​ፈስ አለች፤ በጥ​ፋ​ታ​ቸው መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ዟ​ታል፤ በዘ​መ​ና​ቸው ኀይ​ላ​ቸው ይደ​ክ​ማል፤ የፈ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው መቅ​ሠ​ፍ​ትም ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል።

29 እሳት፥ በረድ፥ ረኃ​ብና ቸነ​ፈር ይህ ሁሉ ለበ​ቀል ተፈ​ጠረ።

30 የም​ድር አራ​ዊት ጥርስ ጊን​ጥና እፉ​ኝት፥ ጦርም ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ታጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተፈ​ጠ​ረች።

31 እርሱ ግን በይ​ቅ​ር​ታው ደስ ያሰ​ኛል፤ የዓ​ለ​ም​ንም መፍ​ቅድ ያዘ​ጋ​ጃል። ሁሉም ጊዜው ከደ​ረሰ ከዕ​ድ​ሜው አያ​ል​ፍም።

32 ስለ​ዚህ ነገር ከጥ​ንት ጀምሮ ሁሉም ተዘ​ጋጀ፤ ይህ​ንም አስቤ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፍ​ሁት።

33 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ሁሉ ያማረ ነውና፤ ለሰ​ውም በየ​ጊ​ዜው መፍ​ቅ​ዱን ይሰ​ጣል።

34 “ይህን ክፉ ፈጠ​ርህ፤ ያንም አሳ​መ​ርህ” የሚ​ለው የለም። ሁሉን ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋ​ልና።

35 አሁ​ንም በፍ​ጹም ልቡ​ና​ችሁ፤ በፍ​ጹ​ምም አን​ደ​በ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ሁል​ጊ​ዜም ለስሙ ምስ​ጋና አቅ​ርቡ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos