Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ተግሣጽ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ልባም ሴትን ማን ያገኛታል? ዋጋው ብዙ ከሆነ ከከበረ ዕንቍ እጅግ የከበረች ናት። 2 እንደዚህ ባለችዋ ሴት የባልዋ ልብ ይታመንባታል፥ እንዲህ ያለችው ሴትም ከመልካም ምርኮ አታሳንሰውም። 3 ዕድሜዋን ሙሉ በክፉ ላይ ክፉ ያይደለ፥ በበጎ ላይ በጎ እየሠራች ባሏን ትረዳዋለች። 4 የበግ ጠጕርንና የተልባ እግርን እያባዘተች፥ በእጆችዋ መልካም ትሠራለች። 5 እርስዋ ከሩቅ እንደምትነግድ፥ ሀብትንም ሁሉ እንደምትሰበስብ መርከብ ናት፤ 6 ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰዎችዋ ምግባቸውን ትሰጣለች። ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች። 7 እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች፤ ከእጅዋም ፍሬ ወይንን ትተክላለች። 8 ወገብዋንም በኀይል ትታጠቃለች፥ እጆችዋንም ለሥራ ታወጣለች። 9 ሥራ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች፤ መብራቷ ሌሊቱን ሁሉ አይጠፋም። 10 እጆችዋንም ወደሚጠቅም ሥራ ትዘረጋለች፥ ክንድዋንም ለመፍተል ታበረታለች። 11 እጅዋን ለችግረኛ ትዘረጋለች፥ መሀል እጅዋንም ወደ ድሃ ትዘረጋለች። 12 ባሏ በውጭ የዘገየ እንደ ሆነ በቤት ስላሉት ምንም አያስብም ። ቤተ ሰዎችዋ ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና። 13 ለባሏ እጥፍ ሆኖ ከተፈተለ የተልባ እግር መጐናጸፊያ ትሠራለች፤ ለራስዋም ከነጭ ሐር ልብስን ትሠራለች። 14 ባልዋ በሀገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ፥ በአደባባይ የታወቀ ይሆናል። 15 የበፍታ ቀሚስ እየሠራች ትሸጣለች። ለከነዓናውያንም ድግ ትሸጣለች። ሕጋዊ በሆነ ነገር አፍዋን ትከፍታለች፤ ለአንደበቷም መጠንን ታደርጋለች። 16 ብርታትንና ውበትን ትለብሳለች፤ በኋላም ዘመን ላይ ደስ ይላታል። 17 ወደ ቤትዋ የሚገባ ብዙ ነው፥ የስንፍና እንጀራንም አትበላም። 18 ሕግና ምጽዋት በአፍዋ አለ፥ አፍዋን በጥበብና ሕግ ባለው ሥርዐት ትከፍታለች። 19 ምጽዋቷ ልጆችዋን ያሳድጋል፥ ያበለጥጋልም፤ ባልዋም እንዲህ ሲል ያመሰግናታል፦ 20 “ብዙ ሴቶች ልጆች ሀብትን ሰበሰቡ፤ ብዙዎቹም ኀይልን አደረጉ፤ አንቺ ግን ትበልጫለሽ፥ ከሁሉም ትልቂያለሽ።” 21 ውበት ሐሰት ነው፥ ደምግባትም ከንቱ ነው፤ ብልህ ሴት ግን ትባረካለች። እግዚአብሔርንም የምትፈራ እርስዋ ትመሰገናለች። 22 ከከንፈሯ ፍሬ ስጡአት፥ ባሏም በአደባባይ ይመሰገናል። |