Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽ​ሐፈ ተግ​ሣጽ 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አን​ገ​ቱን ካደ​ነ​ደነ ሰው ይልቅ፥ የሚ​ዘ​ልፍ ሰው ይሻ​ላል። ድን​ገት ይቃ​ጠ​ላ​ልና፥ፈው​ስም የለ​ው​ምና።

2 በጻ​ድ​ቃን መመ​ስ​ገን ሕዝ​ቦች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ክፉ​ዎች ገዢ​ዎች በሚ​ሆ​ኑ​በት ጊዜ ግን ሰዎች ያለ​ቅ​ሳሉ።

3 ጥበ​ብን በሚ​ወ​ድድ ልጅ አባቱ ደስ ይለ​ዋል፤ ጋለ​ሞ​ቶ​ችን የሚ​ከ​ተል ግን ሀብ​ቱን ያጠ​ፋል።

4 እው​ነ​ተኛ ንጉሥ ሀገ​ሩን ያጸ​ናል፤ ዐመ​ፀኛ ሰው ግን ያፈ​ር​ሰ​ዋል።

5 በወ​ዳጁ ፊት ወጥ​መ​ድን የሚ​ያ​ዘ​ጋጅ ሰው የራ​ሱን እግ​ሮች በው​ስጡ ያገ​ባል።

6 በክፉ ሰው ዐመፃ ወጥ​መድ ይበ​ዛል፤ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም በታ​ላቅ ወጥ​መድ ይወ​ድ​ቃል፥ ጻድቅ ግን በደ​ስ​ታና በሐ​ሴት ይኖ​ራል።

7 ጻድቅ የድ​ሆ​ችን ፍርድ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ ኃጥእ ግን ዕው​ቀ​ትን አያ​ስ​ተ​ው​ልም። ለድ​ሃም ዕው​ቀት ያለው ልቡና የለ​ውም።

8 ክፉ​ዎች ሰዎች ከተ​ማን ያቃ​ጥ​ላሉ፤ ጠቢ​ባን ግን ቍጣን ይመ​ል​ሳሉ።

9 ጠቢብ ሰው ሕዝ​ብን ይገ​ዛል፥ ክፉ ሰው ግን ይቈ​ጣል፥ ይሥ​ቁ​በ​ታ​ልም፥ ነገር ግን አያ​ሳ​ዝ​ነ​ውም።

10 ደምን ለማ​ፍ​ሰስ የሚ​ተ​ባ​በሩ ሰዎች ጻድ​ቁን ሰው ይጠ​ላሉ፥ ቅኖች ግን ነፍ​ሱን ይሻሉ።

11 አላ​ዋቂ ሰው ቍጣ​ውን ሁሉ ያወ​ጣል፤ ጠቢብ ሰው ግን ድር​ሻ​ውን እንኳ በከ​ፊል ያስ​ቀ​ረ​ዋል።

12 ንጉሥ ሐሰ​ተኛ ነገ​ርን ቢያ​ደ​ምጥ፥ በእ​ርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዐመ​ፀ​ኞች ይሆ​ናሉ።

13 አበ​ዳ​ሪና ተበ​ዳሪ በተ​ገ​ናኙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ቱን በአ​ን​ድ​ነት ይጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋል።

14 ለድ​ሆች በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ርድ ንጉሥ፥ ዙፋኑ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።

15 በት​ርና ተግ​ሣጽ ጥበ​ብን ይሰ​ጣሉ፤ ስሕ​ተ​ተኛ ብላ​ቴና ግን ቤተ ሰቦ​ቹን ያሳ​ፍ​ራል።

16 ኃጥ​ኣን ሲበዙ ኀጢ​አት ትበ​ዛ​ለች፤ ጻድ​ቃን ግን በክ​ፉ​ዎች ውድ​ቀት ይፈ​ራሉ።

17 ልጅ​ህን ቅጣ፥ ዕረ​ፍ​ት​ንም ይሰ​ጥ​ሃል፤ ለነ​ፍ​ስ​ህም ክብ​ርን ይሰ​ጣ​ታል።

18 ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ሕዝብ አስ​ተ​ማሪ የለ​ውም፤ ሕግን የሚ​ጠ​ብቅ ግን ብፁዕ ነው።

19 ክፉ አገ​ል​ጋይ በቃል አይ​ገ​ሠ​ጽም፤ ቢያ​ውቅ እንኳ አይ​ታ​ዘ​ዝ​ምና።

20 በቃሉ የሚ​ቸ​ኩ​ለ​ውን ሰው ብታይ፥ ከእ​ርሱ ይልቅ ለአ​ላ​ዋቂ ተስፋ እን​ዳለ ዕወቅ።

21 ቸል​ተኛ ሰው ከሕ​ፃ​ን​ነቱ ጀምሮ አገ​ል​ጋይ ይሆ​ናል፤ በኋላ ግን ራሱን ያሳ​ዝ​ናል።

22 ቍጡ ሰው ጠብን ይጭ​ራል፥ ወፈ​ፍ​ተኛ ሰውም ኀጢ​አ​ትን ያበ​ዛል።

23 ትዕ​ቢት ሰውን ያዋ​ር​ደ​ዋል፥ ሕሊ​ና​ውን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብር ያቀ​ር​በ​ዋል።

24 ከሌባ ጋር የሚ​ካ​ፈል ነፍ​ሱን ይጠ​ላል፤ መሐ​ላ​ንም ቢያ​ወ​ር​ዱ​ለት ይም​ላል፤ አይ​ና​ገ​ር​ምም።

25 በመ​ፍ​ራ​ትና በማ​ፈር ሰው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መን ግን ደስ ይለ​ዋል። የሰው ኀጢ​አቱ በደ​ለኛ ያሰ​ኘ​ዋል፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ሰው ግን ይድ​ናል።

26 ብዙ ሰዎች ለመ​ኳ​ን​ንት ፊት ይላ​ላ​ካሉ፤ የሰው ፍርዱ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።

27 እው​ነ​ተኛ ሰው በግ​ፈኛ ሰው ዘንድ የተ​ናቀ ነው፤ ቀና መን​ገ​ድም በኃ​ጥ​ኣን ዘንድ አስ​ጸ​ያፊ ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos