Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ያዕቆብ INTRO1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1

መግቢያ
ይህ የያዕቆብ መልእክት ለዕለታዊ ኑሮ መመሪያ የሚሆኑ ሐሳቦችን ያዘለ ሲሆን የተጻፈውም በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ዐሥራ ሁለት ነገዶች ነው፤ ጸሐፊው ጥበብን በተግባር ስለምናውልበት ዘዴ፥ ለክርስቲያናዊ አቀባበልና ጠባይ መመሪያ የሚሆኑ ነገሮችን ግልጥ በሆኑ ሥዕላዊ አነጋገሮች ያቀርባል፤ ስለ ድኽነትና ስለ ሀብት፥ ስለ ፈተና፥ ስለ መልካም ጠባይ፥ ስለ ቅናት፥ ስለ እምነትና በጎ ምግባር፥ ስለ አንደበት ጠቃሚነትና ጐጂነት፥ ስለ ጥበብ፥ እርስ በርስ ስለ መጣላት፥ ስለ ትዕቢትና ስለ ትሕትና፥ በሌሎች ላይ ስለ መፍረድ፥ ስለ ትምክሕት ስለ ትዕግሥትና ስለ ጸሎት፥ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት ስለሚገባቸው ግዴታ በዝርዝር ጽፎአል።
መልእክቱ በክርስትና ሕይወት እምነት በተግባር ስለሚተረጐምበት ሁኔታ አጒልቶ ያሳያል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1
እምነትና ጥበብ 1፥2-8
ድኽነትና ሀብት 1፥9-11
ፈተና 1፥12-18
የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና ማድረግ 1፥19-27
አድልዎ እንዳይደረግ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ 2፥1-13
እምነትና ሥራ 2፥14-26
ክርስቲያንና አንደበቱ 3፥1-18
ክርስቲያንና ይህ ዓለም 4፥1—5፥6
ስለ ተለያዩ ነገሮች የተሰጠ ምክር 5፥7-20

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos