Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ጴጥሮስ INTRO1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1

መግቢያ
ሁለተኛው የሐዋርያው የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው በልዩ ልዩ ስፍራ ለሚገኙ የጥንት ክርስቲያኖች ነው። የመልእክቱ ዋና ዓላማ የሐሰተኞች መምህራንን ክፉ ሥራና የእነርሱንም ትምህርት አስመልክቶ የተከሠተውን የብልግና ሕይወት መቃወም ነው። ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሔ የሚሆነው ኢየሱስን በዐይናቸው ያዩትና ሲያስተምርም በጆሮአቸው የሰሙት ሰዎች ባስተላለፉት ትምህርት አማካይነት ስለ እግዚአብሔርና ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተጨባጭ ዕውቀት ማግኘት ነው። ጸሐፊው በተለይ ጥንቃቄ ያደረገው “ክርስቶስ ተመልሶ አይመጣም” ስለሚለው የሐሰት ትምህርት ነው፤ ይህንኑ አስመልክቶ ሲናገር “ክርስቶስ ተመልሶ ከመምጣት የሚዘገየው እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ ማንም ሰው እንዲጠፋ ስለማይፈልግ ነው” ይላል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
የክርስቲያን ጥሪ 1፥3-21
ሐሰተኞች መምህራን 2፥1-22
የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት 3፥1-18

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos