2 ዮሐንስ INTRO1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምመግቢያ ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት የተጻፈው በሽማግሌው ሐዋርያ በዮሐንስ ሲሆን የተጻፈውም ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ ነው። ምናልባትም ለአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንና ለአባሎችዋ ሳይሆን አይቀርም፤ ይህ አጭር መልእክት የተጻፈው እርስ በርስ እንዲዋደዱ ለማሳሰብና ከሐሰተኞች መምህራንና ከትምህርታቸውም ለማስጠንቀቅ ነው። አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት መቅድም 1-3 ፍቅር ከሁሉ በላይ ነው 4-6 ስለ ሐሰተኛ ትምህርት ማስጠንቀቂያ 7-11 ማጠቃለያ 12-13 |