Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽ​ሐፈ ጦቢት 9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የሰርጉ በዓል

1 ከዚህ በኋላ ጦብያ ሩፋኤልን ጠርቶ እንዲህ አለው፥

2 “ወንድሜ አዛርያ አራት አገልጋዮችና ሁለት ግመሎችን ይዘህ ወደ ራጌስ ከተማ ተጓዝ፤

3 ወደ ጋባኤልም ቤት ሂድ፥ የገንዘቡን ፊርማ አሳየውና ገንዘቡን ተቀበል፤ ጋባኤልንም ወደ ሰርጉ ግብዣ ከአንተ ጋር ይዘኸው ና፤

4 መቼም እንደምታውቀው አባቴ ቀኖቹን እየቆጠረ ነው፤ አንድ ቀን እንኳ ብዘገይ ብዙ አስጨንቀዋለሁ፤

5 ራጉኤልም እኔን ለማቆየት እንዴት እንደማለ አይተሃል፤ በመሐላው ታስሬአለሁ።” ሰለዚህ ሩፋኤል አራቱን አገልጋዮችና ሁለቱን ግመሎች ይዞ ወደ ሜዶን ወደ ራጌስ ሄደ፤ እዚያም ከጋባኤል ቤት አደሩ። ሩፋኤልም ፊርማውን ሰጠውና የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዳገባና ወደ ሰርጉ ግብዣም እንደ ጠራው ነገረው። ጋባኤልም የገንዘብ ከረጢቶቹን በማኀተም እንደተዘጉ ቆጥሮ አስረከበውና በግመሎቹ ላይ ጫኗቸው።

6 በማግስቱ ጧት በማለዳ ተነሥተው አብረው ወደ ሰርጉ ሄዱ። ወደ ራጉኤልም ቤት ሲገቡ ጦብያን በማዕድ ተቀምጦ አገኙት። ጦብያ በፍጥነት ተነሣና ጋባኤልን ሰላም አለው፤ ገባኤል እያለቀሰ እንዲህ ሲል ባረከው “አንተ ደግ ልጅ፥ የደጉ፥ የጻድቁና የለጋሱ ልጅ! ጌታ የሰማይን በረከት ለአንተና ለሚስትህ፥ ለሚስትህም አባትና እናት ይስጥ፤ የአጎቴን ልጅ የጦቢትን ሕያው አምሳል ያሳየኝ እግዝአብሔር የተባረከ ይሁን።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos