Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ሲራክ INTRO1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)መግቢያ መጽሐፈ ሲራክ የሚለው ርእስ የተወሰደው ከሲራክ 50፥27 መሆኑን መረዳት ይቻላል፦ የኢየሩሳሌም ሰው የሲራክ የልጅ ልጅ፥ የአልዓዛር ልጅ በሆነው በኢያሱ እንደ ተጻፈ ያመለክታል። ደራሲው ከፍተኛ የጥበብ፥ የሕገ ኦሪት፥ የክህነት፥ የቤተመቅደስና የአምልኮ ፍቅር ነበረው። በዘመኑ የነበሩ አንባብያን ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናት፥ ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁ፥ በአይሁድ እምነት እንዲጸኑ፥ መልካም ሥነ ምግባር እንዲላበሱ ይጋብዛል። በመጽሐፉ ውስጥ አያሌ ምሳሌዎችና ፈሊጦች ይገኛሉ። ምሳሌዎቹም ግለሰብን፥ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን ይመለከታሉ፤ እርስ በእርሳቸውና ከአምላክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይዳስሳሉ። ትኩረት ከሚሰጥባቸው ርእሶች መካከል ወዳጅነት፥ ትምህርት፥ ድህነትና ሀብት፥ ሕጎች፥ አምልኮና አያሌ ባህል ነክ ጉዳዮች ይገኙበታል። መጽሐፉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 175 አካባቢ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንደ ተጻፈ ይገመታል። የደራሲው የልጅ ልጅ ኢያሱም ይህንኑ መጽሐፍ ወደ ግሪክ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 117 አካባቢ እንደተረጐመው ይታመናል። ይህንና ተመሳሳይ ፍሬ ሐሳቦችን በመጽሐፉ መቅድም ውስጥ ማግኘት ይቻላል። መጽሐፉን በተለያዩ ርእሶች መከፋፈል ያዳግታል። ምክንያቱም የምሳሌዎቹ ፍሬ ሐሳቦች በሁሉም ክፍሎች ውስጥ የገኛሉና። ሆኖም ከ 1—43 ያሉት ምዕራፎች በአብዛኛው የሥነ ምግባር ጥያቄዎችን ይዳስሳሉ። ከ44፥1—50፥24 ያሉት ምዕራፎች ደግሞ የእስራኤል ታላላቅ የእምነት ሰዎችን የሚያወድስ ክፍልን ያቀርቡልናል። ምዕራፍ 51፥1-12 ደራሲው ለአምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት ክፍል ነው። በምዕራፍ 51፥13-30 ላይ ደግሞ ሰዎች እውነተኛ ጥበብን እንዲሹና እንዲመርጡ አበክሮ ይጋብዛል። ምዕራፍ |