Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ብልህነትና የተፈጥሮ ዕውቀት

1 ችሎታ ላለው ከትልቅ ሰው አትከራከር፤ አለበለዚያ በእጁ ትወድቃለህ።

2 ከሀብታም ሰው ጋር አትጋጭ አለበለዚያ ይጫንኻል፤ ምክንያቱም ወርቅ ብዙዎችን አጥፍቷል። የነገሥታትንም ልቦና መንገድ አስቷል።

3 ከተሟጋች ጋር አትከራከር፤ በእሳቱ ላይ እንጨት አትከምር።

4 አያቶችህን እንዳይሰደቡብህ ከነውረኛ ሰው ጋር አትዘባበት።

5 በኃጢአቱ የሚጸጸተውን ሰው አትውቀሰው፤ ሁላችንም በደለኞች መሆናችንን አስብ።

6 ሽማግሌን አትጥላ፥ ከኛም አንዳንዶቻችን እየሸመገልን ነውና።

7 በሌላው ሞት አትደሰት፥ ሁላችንም ሟቾች መሆናችንን አትዘንጋ።


ባህል

8 የጥበበኞችን ንግግር አታቃል፤ ምሳሌዎቻቸውን ተከተል፤ ታላላቆችን የማገልገል እውቀትና ጥበብ ከእነርሱ ትማራለህና።

9 ሽማግሌዎች የሚናገሩትን አታቀል፥ እርሱም የተማሩት ከአባቶቻቸው ነውና፤ ብልህነትንና በአስፈላጊውም ጊዜ መልስ የመስጠት ጥበብን የምትማረው ከነሱ ነው።


ማስተዋል

10 በነበልባሉም ትቃጠላለህና የኃጢአተኛን ከሰል አታቀጣጥል።

11 ለተሳዳቢ አትበገር፥ በቃልህ ሊያጠምድህ ይችላል።

12 ከአንተ ለሚያይል አታበድር፤ ካበደርክም እንደጠፋብህ ቁጠረው።

13 ከችሎታህ በላይ ዋስ አትሁን፥ ከተዋስክ ለመክፈል ተዘጋጅ።

14 ከዳኛ ጋር አትካሰስ፥ ምክንያቱም ለእርሱ ይፈረድለታል።

15 ከችኩል ሰው ጋር አትጓዝ፥ አለበለዚያ ሸክም ይሆንብሃልና፤ እሱ በገዛ ፈቃዱ የሚመራ ነው፤ በእርሱም ጥፋት ሁለታችሁም አብራችሁ ትጠፋላችሁ።

16 ከቁጡ ሰው ጋር አትከራከር፤ ሰዎች በሌሉበት ከሱ ጋር አትሂድ፥ ደም መፍሰስ ለእርሱ ምኑም አይደለምና፤ ሰው በሌለበት ሊጎዳህ ይችላል።

17 ከሞኝ ምክር አትጠይቅ፥ ምስጢር መቋጠር አይችልምና።

18 ምን እንዲሆን አታውቅምና በእንግዳ ፊት ምሥጢር አታውጣ። እንግዳው እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አታውቅምና።

19 ለማንም ልብህን አትግለጥ፤ መልካም ተግባሮቻቸውም ላይ አትተማመን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos