Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


በፈተና ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት

1 ልጄ ሆይ ጌታን ማገልገል ስትፈልግ፤ እራስህን ለፈተና አዘጋጅ፤

2 ቅን ልብ ይኑርህ፥ ቆራጥ ሁን፥ በጭንቀት ጊዜ አትታወክ፥

3 ወደ እግዚአብሔር ተጠጋ፥ ከሱ አትራቅ፥ በመጨረሻ ቀኖችህም ክብርን ትጐናጸፋለህ።

4 የሚመጣብህን ነገር ሁሉ ተቀበለው፤ በመከራ ጊዜ ግራ ብትጋባም ታገስ።

5 ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ፥ በእግዚአብሔር የተመረጡ ሰዎችም የሚፈተኑት በውርደት ምድጃ ነው።

6 በእግዚአብሔር ታመን፥ ይረዳሃል፤ ትክክለኛውን መንገድ ተከተል፤ ተስፋህም በእርሱ ላይ ይሁን፤

7 እናንተ ጌታን የምትፈሩ ምሕረቱን ተጠባበቁ፤ እንዳትወድቁ ከሱ አትራቁ።

8 እናንተ ጌታን የምትፈሩ በሱ ተማመኑ፤ የሚገባችሁ ዋጋ አይቀርባችሁም፤

9 እናንተ ጌታን የምትፈሩ፥ የእርሱን መልካም ስጦታዎች ደስታንና ምሕረትን ተስፋ አድርጉ።

10 ያለፉትን ትውልዶች ተመልከቱ፥ እዩ፤ እስቲ ማነው በጌታ ተማምኖ ያፈረ?

11 ማነው እግዚአብሔርን በመፍራት ጸንቶ የተጣለ? ማነው እግዚአብሔርን ለምኖ ያልተሰማ? ምክንያቱም እግዚአብሔር ርኁርኀና መሐሪ ነው፤ ኃጢአትን ይቅር የሚልና በጭንቀት ጊዜ የሚያድን ነው።

12 ስንፍና ለሚያጠቃቸው ልቦችና፥ ብርታት ለሌላቸው እጆች ወዮላቸው፤ በሁለት መንገድ የሚሄድ ወላዋይ ኃጢአተኛ ወዮለት።

13 ብርታትና እምነት የሌለው ልብ ወዮለት፤ ምክንያቱም ጠባቂ የለውም።

14 እናንተ ጸንታችሁ ያልኖራችሁ ወዮላችሁ፤ ጌታ ሲጐበኛችሁ ምን ልታደርጉ ነው?

15 ጌታን የሚፈሩ ሰዎች፤ ከቶ ቃሉን አይጥሱም፤ እግዚአብሔርን የሚወዱ መንገዶችን ይጠብቃሉ፤

16 ጌታን የሚፈሩ ሁሉ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ይፈጽማሉ፤ እሱን የሚወዱ በሕጉ ይረካሉ።

17 ጌታን የሚፈሩ ሁልጊዜ ዝግጁ ልብ አላቸው፤ በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥

18 በሰው እጅ ከምንወድቅ በእርሱ እጅ እንውደቅ፤ ምሕረቱ እንደ ታላቅነቱ ነውና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos