Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የምሳሌዎች መድብል የጥበብ ምንጭ

1 የጥበብ ሁሉ መገኛዋ ከጌታ ዘንድ ነው፥ ለዘለዓለምም ከእርሱ ጋር ናት።

2 የባሕርን አሸዋ፥ የዝናምን ጠብታዎች፥ የዘለዓለምን ቀኖች፥ ማን ቆጥሮ ይዘልቃቸዋል?

3 የሰማይን ምጥቀት፥ የምድርን ስፋት፥ የውቅያኖስን ጥልቀት፥ ማን መርምሮ አወቃቸው?

4 ከፍጡሮች ሁሉ በፊት ጥበብ ተፈጠረች፤

5 ብሩህ ማስተዋል ከጥንት አንሥቶ ነበረች።

6 የጥበብ ሥርዋ ለማን ተገለጠ?

7 የጥበብንስ ዘዴና መንገድ ማን አወቃቸው?

8 ጥበበኛ አንድ ብቻ ነው፥ እርሱም እጅግ ያስፈራል፤ በዙፋኑም ላይ ጸንቶ ይኖራል።

9 ጥበብን የፈጠራት ጌታ ራሱ ነው፤ ያያትና የመዘናትም እርሱ ነው፤ በሁሉም ሥራዎቹም ላይ አፈሰሳት።

10 ለሁሉም ሕያው ፍጡር እርሱ እንደወደደው እሱን ለሚወድት ሰዎች ደግሞ እሷን አብዝቶ ሰጣቸው።


እግዚአብሔርን መፍራት

11 ጌታን መፍራት ክብርና ኩራት ነው፤ ደስታና የሐሴት አክሊል ነው፤

12 ጌታን መፍራት ልብን ደስ ያሰኛል፤ ሐሴትንም ይሰጣል። ደስታንና ረጅም ሕይወትንም ይሰጣል።

13 ጌታን የሚፈራ ሰው መጨረሻው ያምራል፤ በዕለተ ሞቱም ይባረካል።

14 የጥበብ መጀመሪያዋ ጌታን መፍራት ነው፤ ለታማኞች በእናታቸው ማሕፀን ከነሱ ጋር ተፈጥራለች።

15 በሰው ዘር ውስጥ ቤቷን መሥርታለች፤ የዘለዓለም መሠረትም ጥላለች፤ ከልጆቻቸው ጋር ታማኝ ሆና ትኖራለች፤

16 የጥበብ ምልአት ጌታን መፍራት ነው፤ በፍሬዎችዋ ሰዎችን ታረካቸዋለች፤

17 ቤቶቻቸውንም በሀብት ትሞላለች፤ ጐተራዎቻቸውንም በምርቶችዋ ትሞላላቸዋለች፤

18 የጥበብ አክሊልዋ ጌታን መፍራት ነው፤ እርሷም ሰላምና ጤና እንዲያብቡ ታደርጋለች።

19 እግዚአብሔር አይቷታል፥ መዝኗታል፤ እውቀትንና ማስተዋልን አዝንሟል፤ የሚያጸኗትንም ሰዎች ክብር ከፍ አደረገው።

20 የጥበብ ሥሩ ጌታን መፍራት ነው፤ ቅርንጫፎችዋም ረጅም ሕይወት ናቸው።

21 እግዚአብሔርን መፍራት ኃጢአትን ያስወግዳል፤ በውስጡ ያደረበትም ቁጣን ሁሉ ያጠፋል።


ትዕግሥትና ራስን መግዛት

22 የኃጢአተኛው ቁጣ ሊያጸድቀው አይችልም፤ የቁጣውም ክብደት ውደቀቱ ነውና።

23 ትዕግሥተኛ ሰው ትክክለኛው ጊዜ እስኪደርስ ሁሉንም ይችላል፤ በስተመጨረሻ ግን ደስታን ያገኛል።

24 እስከ ጊዜው ሐሳቦቹን ይዞ ይቆያል። ሕዝቡም ዓዋቂነቱን ይናገርለታል።


ጥበብና ትክክለኛነት

25 በጥበብ መዝገቦች መካከል የዕውቀት ምሳሌዎች አሉ፤ ነገር ግን መንፈሳዊነት ለኃጢአተኛ የተናቀና የተጠላ ነው።

26 ጥበብን ከፈለግህ ትእዛዛትን ጠብቅ፤ ጌታም የፈለግኸውን ይሰጥሃል።

27 ጌታን መፍራት ጥበብና ትምህርት ነው፤ ታማኝነትና ደግነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።

28 ጌታን ከመፍራት ውጭ አትሁን፤ ሁለትም ልብ ይዘህ ወደ እርሱ አትቅረብ፤

29 በሰዎች ፊት ጋባዥ አትሁን፤ ከንፈሮችህን ጠብቅ።

30 እንዳትወድቅና በራስህ ላይ ውርደትን እንዳታመጣ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ። ልብህ በተንኮል በመሞላቱና ጌታን ባለመፍራትህ እርሱ ምሥጢርህን ይገልጥብሃል፤ በሕዝቡም መሀል ያዋርድሀል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos